ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ “ከኢትዮጵያ በላይ ለሶማሊያ የሞተ አንድም ሀገር የለም፣ መግለጫ ያወጣ ግን አለ” – ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28/2016 ዓ.ም፡- ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሶማሊላንድ ጋር በተያያዘ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ሶማሊያን የሚጎዳ ምንም አይነት አላማ ኢትዮጵያ የላትም፣ ላለፉት አስራ እና ከዘያም በላይ ባሉት አመታት የሶማሊያን ሰላም ለማስፈን በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሊያ ውስጥ የምንሞተው የሶማሊያ ሰላም የእኛ ሰላም ስለሆነ ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ በላይ ለሶማሊያ የሞተ አንድም ሀገር የለም፣ መግለጫ ያወጣ ግን አለ ሲሉ አስታውቀዋል። የሞተ አንድም ሀገር የለም፣ ወደፊትም አይኖርም ብለዋል።

የሶማሊያ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር መጣላት ፍላጎት ያለው አይመስለኝም ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር አብይ ነገር ግን ሶማሊያን እንደ እጃዙር መጠቀም የሚፈልጉ ሀገራት መኖራቸውን አስታውቀዋል።

ለዚያ ደግሞ እኛ አንመችም ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ በሶማሊያ ወንድሞቻችን ላይ ምንም አይነት የከፋ ነገር ለመናገርም ለማድረግም ዝግጁ አይደለንም ብለዋል።

እነዚያ ይሄንን የሚመኙልን ሀገሮች ለአንዳንድ ዲያስፖራ ወንድሞቻችን ሚዲያ እንደከፈቱላቸው ሁሉ ለአንዳንድ ሶማሊያዊያን ወንድሞቻችን የተወሰነ ነገር ሊያደርጉላቸው ይችላሉ ሲሉ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ሊያዋጉን ግን አይችሉም ሲሉ ተደምጠዋል።

ቢያንስ በእኛ በኩል አንዋጋም፣ እኛ እምንፈልገው ሶማሊያ አድጋ ለኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ ሁና ተጠቅማ ስትጠቅም ማየት ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ለሶማሊያ አንድነት እንደእዚህ መንግስት የሰራ የለም ሲሉ የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ ሶማሊያ እና ሶማሊላንድን ለማገናኘት ጥረናል፣ ሁለቱ ቢስማሙ የመጀመሪያው ተደሳች ሀገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአለም ህግ፣ በቢዝነስ ህግ መዳኘት እንፈልጋለን ሲሉ አሳስበዋል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button