ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአስመራ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር የተለየ ንግግር እና ምክክር አልነበረም – ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28/2016 ዓ.ም፡- ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባል ተጠይቀው ምላሽ ከሰጡባቸው ጥያቄዎች መካከል በሀገሪቱ በተለይ በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ስላሉ ግጭቶች እና ሰላም እጦትን የተመለከቱት ይገኙበታል።

በሀገራችን በተለያየ ስፍራ በሚገባም በማይገባም በቀላል ሊፈታ በሚችል ምክንያት ሁሉ ጦርነት ግጭት መፈናቀል ይታያል ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኦሮምያ ክልልን በተመለከተ

በኦሮምያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ጠ/ሚኒስትሩ ሸኔ እያሉ ሲጠሩት የተደመጠው) እና በመንግስት መካከል ከመጀመሪያው ጀምሮ ምንም የተለየ ስምምነት አልነበረም ሲሉ የተደመጡት ጠ/ሚኒስትር አብይ  በወቅቱ ከመንግስታቸው የቀረበው የኢትዮጵያ ተፋላሚ ሀይሎች ከያሉበት ሀገር ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የሀሳብ ትግል እናዲያደርጉ የሚል ብቻ እንደነበር ጠቁመዋል፤ ለኦነግ የቀረበው ጥሪ ለኦብነግ፣ ግንቦት 7 ከቀረበው ጥሪ የተለየ አልነበረም ሲሉ ተደምጠዋል።

ከሸኔ ጋር የሚደረግ ድርድር ግልጽ አይደለም፣ ምን ተስማምታችሁ ነው ወደ ሀገር ውስጥ የመጡት? ምን ቃል ተገብቶላቸው ሳይመለስላቸው ቢቀር ነው ወደ ግጭት ያመሩት? የሚል ጥያቄ ከያቅጣጫው እንደሚነሳ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትሩ ከኦነግ ጋር የተለየ ንግግር እና ምክክር አልነበረም ብለዋል።

አሁን ሸኔ ተሰማርቶ ያለው “ግለሰቦች ማገት፣ መኪና ማቃጠል፣ ልማት እንዳይሰራ ማድረግ” ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትር አብይ ይህ በማንኛውም የትግል መስፈርት ለሆነ አላማ ማሳኪያ የሚደረግ የትግል ስልት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፤ ጥፋት ነው ብለዋል።  

“እንካችሁ ውሰዱ ቢባሉ፣ ስልጣን ቢሰጠው በምን ሞራል ነው የገደልከውን፣ ያገትከውን ህዝብ ልምራህ የምትለው” ሲሉ በመጠየቅ “ልቦና ገዝቶ ወደ ሰላም መድረክ ማምጣት ያስፈልጋል” ሲሉ አሳስበዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አማራ ክልልን በተመለከተ

ከአማራ ክልል ከከሚሴ በስተቀር በሁሉ ዞኖች ከነዋሪዎች ጋር የመወያየት እድል እንደነበራቸው ገልጸው በሁሉም በሚባል መልኩ የሚነሱ ሶስት ጥያቄዎች ነበሩ፤ አንድ የልማት ጥያቄ ተጎድተናል ወደ ኋላ ቀርተናል ልማት የለም የሚል፣ ሁለት የህገመንግስት ጥያቄ ህገመንግስቱ አግልሎን ተነስቷል፣ ማሻሻያ ያስፈልገዋል የሚል እና በሶስተኝነት የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የሚል ነው ብለዋል።

የክልሉን የልማት ጥያቄ መንግስት ባለው አቅም በርካታ ስራዎችን ሰርቷል ሲሉ የዘረዘሩት ጠ/ሚኒስትሩ በአብነትም ባለፉት አምስት አመታት የክልሉን ዞኖች እና ወረዳዎችን የሚያገናኙ 3ሺ 200 ኪሜ የሚሸፍን 53 የመንገድ ፕሮጀክቶች ቀርጸን ስራ ጀምረናል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ 1ሺ 300 ኪሜ ተጠናቆ ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የህገመንግስት ማሻሻልን በተመለከተ፣ ለትውልድ የሚሻገር ህገመንግስት ለመቅረጽ እንዲቻል ሀገራዊ ምክክር ተጀምሯል፤ በኮሚሽኑ በኩል የአማራ ክልል ሁለተኛው ጥያቄ ምላሽ ያገኛል ብለዋል።

የወሰን ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በትግራይም በአማራም በኩል ያሉ የይገባኛል ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ያሰብነው ዘላቂ ሰላምን በሚያረጋግጥ መንገድ ነው ሲሉ አስታውቀው “ትግራይ ነጥቄ በጉልበት ልያዘው ቢል፣ አማራም ነጥቄ በጉልበት ልያዘው ቢል” የግዜ ጉዳይ እንጂ ዘላቂ የሆነ ሰላም ማምጣት አይቻልም፤ ያለው መፍትሄ በሰከነ መንገድ የሀገር ሽማግሌዎች ሙሁራን ተሳትፈውበት በውይይት በንግግር ሰላምን በሚያረጋግጥ መልኩ እንፍታው የሚል ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

ሪፈረንደም እስኪካሄድ በሚል መንግስት ምላሽ ያስፈልጋቸው ብሎ የለያቸውነ ጉዳዮች የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትሩ አንደኛ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው ይመለሱ፣ ሁለተኛ የተመለሱ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አከባቢዎች ህዝብ እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር፣ ሶስተኛ የሁለቱም ክልሎች ሙሁራን የሀይማኖት አባቶች ወጣቶች እንዲወያዩ በማድረግ በሪፈረንደም ህዝቡ ወደሚፈልግበት እንዲካለል ይደረግ የሚሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልልን በተመለከተ

ከፕሪቶርያው ስምምነት የፌደራል መንግስት እና የክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር በጋራ በጣም ትላልቅ ድሎች አስመዝግበዋል ሲሉ የገለጹት ጠ/ሚኒስትር አብይ የሚቀሩ ያልተሟሉ ስራዎች ግን አሉ ሲሉ አምነዋል። ከስኬቶቹ መካከል አየር መንገድ ግማሽ ሚሊየን ብር አውጥቶ ጥገናዎችን በማድረግ ወደ ክልሉ በረራ መጀመሩን፣ 217 ፋብሪካዎች ስራ መጀመራቸውን የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል የሚሰጡ 500 ትራክተሮች ገዝቶ ጂቡቲ መድረሳቸውንም አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button