ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ

እለታዊ ዜና፡ ፋኖ ጦርና ጋሻ ይዞ ለኢትዮጵያ ነፃነት የሚሰለፍ እንጂ የሀገሩ ሰራዊት ላይ ጦር የሚመዝ አይደለም- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26/ 2015 ዓ.ም፡- የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፋኖ ሀገር ተወረረች ሲባል ጦርና ጋሻ ይዞ ለኢትዮጵያ ነፃነት የሚሰለፍ እንጂ መልሶ የሀገሩ ሰራዊት ላይ ጦር የሚመዝ አይደለም ሲሉ ተናገሩ፡፡ ኢታማዦር ሹሙ ይህ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከመከላከያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የተከበረውን የፋኖ ስም መጠቀሚያ በማድረግ በስሙ እየተንቀሳቀሰ ያለው ኃይል በዘረፋ ተግባር ላይ የተሰማራና መንገዶችን በመዝጋት የህዝቡን ሰላም የሚያወክ ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡

በአማራ ክልል የህዝቡን የመብት ጥያቄ ካባ በማድረግ ፍላጎቱን በኃይል ለማሳካት የተንቀሳቀሰው ኃይል ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጅ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

ኢታማዦር ሹሙ “ይህ ህዝቡን ሰላም ሲነሳ የነበረው ኃይል የሰራው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መልሶ እርቃኑን እንዲቀር እንዳደረገውና ይህን ኃይልም የመከላከያ ሰራዊቱ እግር በእግር እየተከታተለና እያሳደደው ነው፤ አሁን ከህዝቡ እየተነጠለ ነው ያለው ኃይሉ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች አቅሙን በማዳከም ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ላይ ድርሷል” ሲሉ ገልፀዋል።

አገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆነው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሚነዙ ኃይሎች ለሀገርና ለህዝብ ሲል ውድ ህይወቱን እየከፈለ ሰላም የሚያረጋግጠውን ሰራዊት ስነ-ልቦና ያልተረዱ ናቸው ያሉት ኢታማዦር ሹሙ ሰራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በአስተማማኝ እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

የፅንፈኞች የሀሰት ፕሮፖጋንዳን የተገነዘበው ህዝባችን ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን ለሰላሙ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሀሰተኞች ሴራ ተታለው “ፅንፈኞች” ካሏቸው አካላት ጋር የተሰለፉ ወጣቶች በሰላማዊ መንገድ ወደ ህዝቡ እንዲመለሱም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button