ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የኢትዮ ኒውስ ዋና አዘጋጁ በላይ ማናየ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25/2016 ዓ.ም፡- የጋዜጠኛ ተቆርቋሪ ተቋም የሆነ ሲፒጄ ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትበት በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮ ኒውስ ዩቲዩብ ሚዲያ ዋና አዘጋጁ በላይ ማናየ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈታ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።

ሲፒጄ ጋዜጠኛ በላይ ማናየ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ያለምንም ክስ እና ማብራሪያ በእስር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሀይሎች እና የሲቪል ልብስ የለበሱ የድህንነት ሰዎች በኢትዮ ኒውስ ጽ/ቤት አቅራቢያ ጋዜጠኛ በላይ ማናየን አስረው እንደወሰዱት ባለቤቱ በላይነሽ ንጋቱ እና የኢትዮ ኒውስ ሌለኛው መስራች በለጠ ካሳ እንደነገሩት ሲፒጄ በመግለጫው አመላክቷል።

የጸጥታ ሀይሎቹ በላይን ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደወሰዱት የጠቆመው ሲፒጄ እስካሁን ለምን ለእስር እንደተዳረገ የተገለጸለት ነገር አለመኖሩን አስታውቋል።

ጋዜጠኛ በላይ ማናየ ያለምንም ማብራሪያ ላለፉት ሶስት ሳምንታት በእስር ቤት እንደሚገኝ የገለጸው ሲፒጄ ይህም በማንኛውም ሰዓት ነጻነታችሁ ሊገፈፍ ይችላል የሚል ለሌሎች የሀገሪቱ ጋዜጠኞች የከፋ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ የተቋሙ የአፍሪካ የሰሃራ በታች ተወካይ የሆኑት ሙቶኪ ሙሞ መናገራቸውን አካቷል።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ በላይ ማናየን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱት እና የጋዜጠኞች የዘፈቀደ እስር እንዲቆም ተወካዯ መናገራቸውን ሲፒጄ በመግለጫው አመላክቷል።

በላይ ማናየ ታስሮበት በሚገኘው እስር ቤት ድረስ በመሄድ የጠየቀችው ባለቤቱ በላይነሽ ለእስር የተዳረገው በአማራ ክልል የተነሳውን ግጭት ተንተርሶ የታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ይሆናይ ያሰሩኝ ሲል እንደገለጸላት መናገሯን መግለጫው ጠቁሟል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button