ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ችግር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይገኛል ተባለ፣ 4 ሚሊየን ህዝብ ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጡም ተጠቁሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ በበርካታ ቦታዎች የምግብ ዋስትና ችግር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን በድርቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ላይ የሚሰራው ፊውስ ኔትወርክ የተሰኘ ተቋም ያወጣው ሪፖርት አመላከተ።

አስፈላጊ ድጋፍ ካልተደረገ በስተቀር እስከ ቀጣይ ሰኔ ወር ድረስ በሀገሪቱ አምስት ክልሎች የሚገኙ ከአራት ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡ ይሆናሉ ሲል ስጋቱን አስቀምጧል።  

ተቋሙ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብሎ ከመደባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት ያለው የድርጅቱ መግለጫ ኤሊኖ ያሳደረው የአየር ንብረት ተጽእኖ እና በሀገሪቱ እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች  በግብርና ምርቶች መቀነስ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ማሳደራቸው ጠቁሞ በህብረተሰቡ ዘንድ አሳሳቢ የኢኮኖሚ ችግር መፈጠሩን አስታውቋል።

ባለፉት ሶስት አመታት የትግራይ፣ አፋር አማራ እና ኦሮምያ ክልሎች በርካታ አከባቢዎች በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ዋስትና ችግር ተስተውሎባቸው እንደነበር የጠቆመው ድርጅቱ በእነዚህ አከባቢዎች የሚገኙ የቤተሰብ አባላት የነፍስ ወከፍ የምግብ ፍጆታ በእጅጉ እያሽቆለቆለ እንደሚገኝ አመላክቷል።

ትግራይን ሳይጨምር በመላ ሀገሪቱ ሶስት ነጥብ ሶስት ሚሊየን ሰዎች በድርቅ እና በግጭቶች ሳቢያ መፈናቀላቸውን ያስታወቀው የድርጅቱ ሪፖርት ህጻናቱ በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተጠቁ መሆናቸውንም አመላክቷል።

በአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ አከባቢ ባለፉት ሶስት አመታት ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ በርካታ የቁም እንስሳት መሞታቸውን ተከትሎ የአከባቢው ነዋሪዎች ለማገገም ብዙ አመታት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁሟል።

በኦሮምያ እና ሶማሊያ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ከ20 በመቶ በላይ የሚሆኑት የቤተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ወይንም ደግሞ ለተረጂነት የተጋለጡ ሁነዋል ሲል መግለጫው አስታውቋል። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በትግራይ በግጭት ሳቢያ እና በአከባቢው የመኸር ሰብል አለመብቀል ጋር በተያያዘ የከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ያጋጥማል ሲል ስጋቱን አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የምግብ ዋስትና ችግር የተጋለጠባቸውን የቤተሰብ አባላት ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ የምግብ እርዳታ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button