ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነት በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ተካሂዶ የነበረውን ደም አፋሳሽ ጦርነትን ለማስቆም የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት 23ኛ አመትን ምክንያት በማድረግ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የአውሮፓ ህብረት ባወጡት መግለጫ ሀገራቱ ለስምምነቱ ተግባራዊነት በጋራ እንዲሰሩ ጠየቁ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የአውሮፓ ህብረት በተናጠል ባወጡት መግለጫ ሁለቱም ለአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነት የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ በድጋሚ ቃል ገብተዋል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላማቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት እና ቀጠና የበለጸገና የተረጋጋ እንዲሆን የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያበረታቱም አስታውቀዋል።

በ2018 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በፈፀሙት ታሪካው የሰላም ስምምነት በአልጀርሱ ስምምነት የተቀመጡትን የድንበር ማካለሎች ለማክበር በድጋሚ ቃል መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውሷል። የአውሮፓ ህብረት በመግለጫው በስምምነቱ መሰረት ከምንግዜም በላይ የሀገራቱ ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት ሊያከብሩ የሚገባበት ወቅት ነው ሲል አሳስቧል።

ከ23 አመታት በፊት ታህሳስ ወር በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተፈረመው የአልጀርሱ ስምምነት የጦርነቱ መነሻ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ የሆነውን የድንበር መካለል ለማስፈጸም ያለመ እንደነበር ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button