ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኢትዮጵያና ጅቡቲ ስራ አጥነትን መቅረፍ ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች በጋራ እንሰራለን አሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11/2016 .ም፡ የጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ድልኤታ መሀመድ ድልኤታ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባው በመገኘት ንግግር ማድረጋቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ኢትዮጵያና ጅቡቲ ስራ አጥነትን ጨምሮ መሰል የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ተመሳሳይ በመሆናቸው የሚጋጥሙ ችግሮችን በትብብር እና ተቀራርቦ በመስራት ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

እስካሁንም ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር በባቡር፣ በንጽሑ መጠጥ ውሀ፣ በፋይበር ኦብቲክስ ዙሪያ በጋራ እየሰሩ መሆኑን አመላክተው በአረንጓዴ አሻራ፣ በዲጂታል ሚዲያ፣ የልምድ ልውውጥ በማድረግና በስፖርት የተጀመሩ ተግባራትን የበለጠ የማጠናከር ስራ እንደሚሰራና ይህም የሁለቱን ሀገራት ትስስር ይበልጥ እንደሚጠናክርም አብራርተዋል።

በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ያሉት ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንኙነቶች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ፕሬዝዳንቱ መግለጻቸውን ያሳትወቀው ምክር ቤቱ ያጋራው መረጃ ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በባህል፣ በስነ-ጽሁፍ፣ በቱሪዝም፣ በስፖርት፣ እንደ ኢጋድ ያሉ አህጉራዊ ድርጅቶችን በማጠናከር ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ታላቅ ሀገር ናት ሲሉ ማወደሳቸውንም አካቷል።

ፕሬዝዳንቱ የጉብኝታቸው ዋናው ዓላማ አሁንም ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር በበርካታ ዘርፎች ያላትን ግንኙነትንና አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሆነም መናገራቸውን አመላክቷል።

በትላንትናው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ከጅቡቲ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት ኘሬዚዳንት ዲልታ መሐመድ ዲልታ በጽ/ቤታቸው ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁለቱ ምክር ቤቶች በትብብር ለመስራት መምከራቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያላት ግንኙነት መልካም መሆኑን አፈ ጉባዔው ጠቁመዋል ያለው የምክር ቤቱ መረጃ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በኢጋዲ ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሁለቱ አገራት ምክር ቤቶች በትኩረት መሥራት አለባቸው ማለታቸውንም አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በፕሬዝዳንት ዲሌታ መሐመድ ዲልታ የተመራው የጂቡቱ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ መጎብኘቱን የጠቆመው ምክር ቤቱ ልዑካን ቡድኑ ባደረገው ጉብኝትም በአውሮኘላን ጥገና፣ በጭነት /ካርጎ/፣ በምስለ በረራ ክፍል እና በአቬሽን ዩኒቨርስቲ እንዲሁም በቦይንግ ኩባንያ ምርት አቅራቢ በሆነው ስካይ ቴክኖ በተባለው ድርጅት በመገኘት ምልከታ ማድረጉን አመላክቷል።

ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ለመሆን ለጎረቤት ሀገራት አየር መንገዱን ጨምሮ በርካታ የሀገሪቱ ሀብቶች ላይ ድርሻ መስጠት እንደምትፈልግ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መናገራቸው ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button