ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በኢትዮጵያ “ድርቅ እንጂ ረሃብ” አልተከሰተም ሲል መንግስት አስተባበለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11/2016 .ም፡ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ወደ ረሃብ ተቀይሯል የሚሉ መረጃዎች ሌላ ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት የሚያዘዋውሯቸው እንጂ ሣይንሳዊና እውነተኛ መሠረት የላቸውም ሲሉ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ገለጹ።

በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ነው የሚል መረጃ በማሠራጨት ላይ ያሉ ወገኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ ኮሚሽነሩ ማሳሰባቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

ድርቁ ከተከሰተ በኋላ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን በመግለጽ አጋር ተራድዖ ድርጅቶች ያደረጉትን ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ጨምሮ በአጠቃላይ ለሰብዓዊነት የሚውል የ15 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ድጋፍ አግኝተናል ማለታቸውን ዘገባው አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ለተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መንግሥት 11 ቢሊየን ብር መድቦ እየሠራ ነው ማለታቸውንም አካቷል።  

ድርቁ በአማራ ክልል ባሉ ሥምንት ዞኖች፣ በአፋር ክልል ባሉ ሦስት ዞኖችና በትግራይ ክልል በሚገኙ ሦስት ዞኖች መከሰቱን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል ያለው ዘገባው  ተጎጂዎችን ለመድረስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል ብሏል።

ኮሚሽነሩ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ አሁንም የፀጥታ ችግሮች ፈተና ሁኖብናል ማለታቸውን ዘገባው አካቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button