ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ድንበሮቻቸውን እና የግዛት አንድነታቸውን የሚያስጠብቁበት ግዜ አሁን ነው – ዩናይትድ ኪንግደም

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4/2016 .ም፡ የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቃል አቀባዩ በኩል ባወጣው መግለጫ ከምንግዜውም በላይ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበሮቻቸውን እና የግዛት አንድነታቸውን በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የሚያስጠብቁበት ግዜ አሁን ነው ሲል አሳስቧል።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አካሂደውት የነበረውን ደም አፋሳሽ ጦርነትን ለማስቆም የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት 23ኛ አመትን ምክንያት በማድረግ ዩናይትድ ኪንግደም መንግስት መግለጫ አውጥቷል።

ከ23 አመታት በፊት ሁለቱ ሀገራት በአለም አቀፉ ማህበረሰብ እገዛ ሰላም ለማስፈን እና ድንበራቸውን ለማካለል የአልጀር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ያወሳው መግለጫው ከአምስት አመታት በፊት ይህንን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ሁለቱ ሀገራት በድጋሚ ቃላቸውን ማደሳቸውን አመላክቷል።

መስሪያ ቤቱ በመግለጫው ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከምግዜውም በላይ ድንበሮቻቸውን እና የግዛት አንድነታቸውን በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የሚያስጠብቁበት ግዜው አሁን ነው ሲል አሳስቧል።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ለአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነት ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል። ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጋር ሰላም እና ብልጽግናን ለማስፈን እንዲሁም የጋራ ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆኑን አመላክቷል።

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ተካሂዶ ከነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነትን ለማስቆም የተፈረመውን የአልጀርስ ስምምነት 23ኛ አመትን ምክንያት በማድረግ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የአውሮፓ ህብረት ባወጡት መግለጫ ሀገራቱ ለስምምነቱ ተግባራዊነት በጋራ እንዲሰሩ መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የአውሮፓ ህብረት በተናጠል ባወጡት መግለጫ ሁለቱም ለአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነት የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ በድጋሚ ቃል መግባታቸውን በዘገባችን አካተናል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላማቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት እና ቀጠና የበለጸገና የተረጋጋ እንዲሆን የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያበረታቱም አስታውቀዋል።

በ2018 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በፈፀሙት ታሪካው የሰላም ስምምነት በአልጀርሱ ስምምነት የተቀመጡትን የድንበር ማካለሎች ለማክበር በድጋሚ ቃል መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውሷል። የአውሮፓ ህብረት በመግለጫው በስምምነቱ መሰረት ከምንግዜም በላይ የሀገራቱ ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት ሊያከብሩ የሚገባበት ወቅት ነው ሲል አሳስቧል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button