ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ 90 በመቶ የትግራይ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4/ 2016 ዓ/ም፡ የጦርነት ቀጠና በነበረው ትግራይ ክልል ከ90 በመቶ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የመግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም ምግብ ፕሮግራም አሳሰበ። 

“ከአጠቃላይ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ 91 በመቶ የሚሆኑት በግጭት ምክንያት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ የአለም ምግብ ፕሮግራም ቃላቀባይ ቶምሰን ፒሪ በጄኔቫ ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ዶቸ ቭለ ዘግቧል።

“የአልሚ ምግብ ድጋፍ እና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እጅግ አሳስቦናል” ሲሉም ተናግረዋል።

የቁጥሩን አሳሳቢነት በአጽንዖት የጠቀሰው ተቋሙ በክልሉ የተከሰተውን የረሃብ አደጋ ለመፍታትም 200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋል ሲል ገልጿል። 

ባሳለፍነው ሳምንት አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ በትግራይ የተከሰተውን ረሃብ ለማስወገድ አፋጣኝ እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባ ለጸጥታው ምክር ቤት አሳስበዋል ነው የተባለው። “በቀጣዮቹ ሁለት ወራት እርዳታው ካልተፋጠነ አስከፊ የረሃብ አደጋ ሊኖር ይችላል” ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርክ ሎውኮክ አመላክተዋል።

“ከ90 በመቶ በላይ የመኸር ምርት በዝርፊያ፣ በቃጠሎ ወይም በሌላ ምክንያት ጠፍቷል” ያሉት አስተባባሪው “ 80 በመቶ የሚሆኑ እንስሳትም ተዘረፈዋል ወይም ለምግብነት ውለዋል” ብለዋል።

የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች በተለይም በገጠር አካባቢዎች ደጋፍ ለሚያስፈለጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለመድረስ የሚያደርጉትን ጥረት በአማራ ከልል የተከሰተው አለመረጋጋት እያዳከመው ነው ሲል የአለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በሰሜንምዕራብ እና ደቡብ ትግራይ አካባቢዎች ስርጭት ከተጀመረ በመጋቢት ወር ጀምሮ ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ማድረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button