ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ በዲፕሎማሲ መልስ እንዲያገኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊሰሩ ይገባቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13/2016 .ም፡ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ቀጣና ያላት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ላይ ያተኮረ በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ሰመራ፣ አዲስ አበባ፣ መቐለ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት በሰመራ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአውደ ጥናቱ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ ዲፕሎማሲን በተከተለ መንገድ መልስ እንዲያገኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊሰሩ ይገባቸዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ መናገራቸውን ኢቲቪ በዘገባው አስታውቋል።

ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ኢትየጵያውያን በቅርብ ርቀት ከሚመለከቱት የባህር በር ፍትሐዊ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ጠቅሰው፤ የህዝብ ለህዝብ እና የባህል ዲፕሎማሲን ማሳደግ ከዩኒቨርሲቲዎች ይጠበቃል ብለዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሐመድ ኡስማን ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የባህር በር ለማግኘት ያላትን ትክክለኛ ፍላጎት በማሳወቅና ሌሎች አካላት የሚሰነዝሩትን ሀሰተኛ መረጃ በማክሸፍ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ላይ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ቀጣና ያላት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ቀርበዋል።

ኢትጵዮጵያ ወደብ አልባ በመሆኗ ሸቀጦችን ለማስገባትም ሆነ ምርቶችን ወደ ውጪ ለመላክ ያልዳበረ መሰረተ ልማት ባላቸው ጎረቤቶቿ ላይ ጥገኛ እንድትሆን ማድረጉም ተጠቅሷል።

የቀይ ባሀር ቀጣናን ከፉክክር ወደ ትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት እድሎችን በማሳደግ  የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማረጋገጥና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠንካራ ስራ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ በሚገኘው አውደ ጥናት ላይ ”ድንበር ተሻጋሪ ተፋሰስና ባህር ረገጥ የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት፣ ጂኦፖለቲካና ቀጣናዊ ደህንነት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችንና የባህር ውሃን ለቀጣናዊ ልማትና ለአካባቢው ደህንነት መረጋገጥ ሊጠቀሙበት ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button