ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ መራዘሙ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ፈተና በቀጣይ ቅዳሜ ይሰጣል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12/2016 .ም፡ አጋጥሟል በተባለ የቴክኒክ ችግር ሳቢያ ሳይሰጥ የቀረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ፈተና በቀጣይ ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞችን ብቃት እና ባህሪ ለመመዘን በሚል ከ16 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፈተና እንደሚቀመጡ ቢገለጽም ፈተናው ሳይሰጥ መቅረቱ ይታወሳል።

አስተዳደሩ ፈተናው ያልተሰጠው ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ነው ብሏል። አጋጠመ የተባለው የቴክኒክ ችግር የተፈጠረው የከተማ አስተዳደሩ የምዘና ስራውን እንዲያከናውኑ ሀላፊነት በሰጣቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መሆኑም ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ፈተናውነ ለመውሰድ በመፈተኛ ቦታዎች በመገኘት በትእግስት ሲጠባበቁ የነበሩትን የአስተዳደሩን ሰራተኞች ለደረሰባቸው መጉላላት ቢሮው ይቅርታ ጠይቋል።

አጋጠመ የተባለው ዋነኛ የቴክኒክ ችግሮች ተፈታኞች ስማቸውን ጽፈው ሳይሆን በኮድ የሚፈተኑ በመሆኑ በኮድ አሰጣጥ ላይ ያጋጠመ ችግር መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መግለጻቸው ይታወሳል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button