ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በእስራኤል እና ፍልስጤሙ ሃማስ መካካል በቀጠለው ጦርነት እስካሁን ከ 1300 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28/ 2015 ዓ.ም፡-  ከቅዳሜ መስከረም 26 ጀምሮ በእስራኤል እና ፍልስጤሙ ሃማስ መካካል በቀጠለው ጦርነት እስካሁን ከ 1300 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ከጋዣ ወደ እስራኤል ላይ 5000 ሮኮቶችን ማስወንጨፉን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስት ቤንያሚን ኔታንያሁ “ጦርነት ላይ ነን” ሲሉ ለአለም አስታውቋል፡፡

ሃማስ የሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በወሰደችው የአፀፋ ምላስ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህ ከፍተኛ ውድመት እና መፈናቀልን እያስከተለ ባለው ውጊያ 800 የእስራዔል ዜጎች ሲሞቱ 2243 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በጋዛ በኩል ደግሞ አስራኤል ከቅዳሜ ጀምሮ ጋዛ ሰርጥ ላይ በወሰደችው የሚሳዔል ጥቃት 510 ፍልስጤማዊያን መሞታቸውን እና 2750 ሰዎች መቁሰላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታቋል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት የጋዛን ሰርጥ ለመክበብ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህም የጋዛ ሰርጥ ኤልክትሪክ አገልግሎት፣ ነዳጅ፣ እና ምግብ ያሉ መሰረታዊ ፍጆታዎች አቋርጠናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በእየሩሳሌም ከተማ የሚሰማ የሮኬት ጥቃት ሀማስ ከጋዛ ማስወንጨፍ መቀጠሉን እና አስራኤል ጥቃቱን ተከትሎ በርካታ ዜጎቿ በሃማስ ታፍነው መወሰዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሜጀር ኒር ዱናራንቱ እንዳሉት ሃማስ በእስራኤል ላይ የፈፀመው ጥቃት በ2001 አልቃየዳ በአሜሪካ ላይ ከፈፀመው 9/11 ጥቃት የሚተናነስ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከእስራኤል ጎን እቆማለው ስትል የተሰማችው አሜሪካ በርካታ የጦር መርከቦችን እና አውሮፕላኖችን ወደ እስራኤል እየላቸው መሆኑን አልጄዚራ አስነብቧል፡፡

እስራኤል አጠናክራ እየወሰደች በለችው የአየር ጥቃት 123 ሺህ በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button