ዜናፖለቲካቢዝነስ

ዜና፡ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ በብሪክስ የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ሁነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23/2016 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ በይፋ የብሪክስ አባል መሆኗን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ዕለቱ ታሪካዊ ቀን ነው ሲል ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው የብሪክስ አባልነት በይፋ ለመቀላቀል ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበር አስታውቆ የብሔራዊ ባንክ ገዢ የሆኑትን ማሞ እስመለአለም ምህረቱን የኢትዮጵያ የብሪክስ ዋና ተወካይ አድርጎ መሰየሙን ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ምስጋኑ አረጋው ደግሞ ረዳታቸው ሁነው መሰየማቸውን ጠቁሟል።

ኢትዮጵያ በብሪክስ በሚኖራት ተሳትፎ ገንቢ ሚና እንድትጫወት የሚያስችል ስራዎችን የሚያከናውን ብሔራዊ የሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሚቴ መቋቋሙንም መግለጫው አመላክቷል።

ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ በአባል ሀገራቱ መካከል የጋራ ተጠቃሚነት እንዲጎለብትና የደቡብ ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር እንደምትሰራ ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button