ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የአማራ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ባለፉት 6 ወራት መሰብሰብ የቻለው ገቢ 25 በመቶውን የሚሆነውን ብቻ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20/2016 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል በበጀት አመቱ ስድስት ወራት 71 ቢሊዮን 650 ሚልዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ማሳካት የቻለው 17 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብቻ መሆኑን አስታወቀ። ይህም የእቅዱን 24.7 በመቶ መሆኑን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የዕቅድ አፈፃፀሙ ዝቅ እንዲልም ዋነኛ ምክንያቱ በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር መሆኑን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ሃላፊው አቶ ፍቅረ ማርያም ደጀኔ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸጸምን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

የበአማራ ክልል ገቢወች ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቅረ ማርያም ደጀኔ ክልሉ በበጀት አመቱ ከመደበኛ ገቢ 56 ቢሊዮን 150 ሚልዮን ብር፣ ከተማ አገልግሎት ገቢ 15 ቢሊዮን 500 ሚልዮን፣ በድምሩ 71 ቢሊዮን 650 ሚልዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከመደበኛ ገቢ 16 ቢልዮን 319 ሚልዮን ብር ፣ ከተማ አገልግሎት 1 ቢሊዮን 38 ሚሊዮን ብር፣ በድምሩ 17 ቢሊዮን 7 መቶ ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 24.7 ፐርሰንት መፈፀም መቻሉን ጠቁመዋል።

በክልሉ ለታየው የግብር አሰባሰብ አፈጻጸም ማነስ የጸጥታ ችግር ዋነኛ ምክንያት ቢሆንም በተመሳሳይ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር እንደ ሽፋን በመጠቀም ግብር ከፋዮች ወቅቱን ጠብቀው ግብር መክፈል አለመቻላቸው፣ በሀሰተኛ ደረሰኞች ግዥ በማቅረብ ለማጭበርበር ጥረት መደረግ፣ በተመሳሳይ ድርጅት ላይ ፈቃድ በመቀያየር እና ግብር በመሰወር እንዲሁም ለሸጡት እቃ ለተጠቃሚው ደረሰኝ አለመስጠት እና ዘመናዊ አሰራሮችን አለመከተል ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ም/ቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button