ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ከሶስት ቀናት መጉላላት በኋላ ሁለት ሺ 200 የሚጠጉ የፀለምት ወረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች እና ተፈናቃዮችን የማስመለስ ሃላፊነት በተሰጣቸው የትግራይ ክልል ባለስልጣናት አለመስማማት ሳቢያ ከሶስት ቀናት መጉላላት በኋላ ሁለት ሺ 200 የሚጠጉ የምዕራብ ትግራይ ዞን ፀለምት ወረዳ ተፈናቃዮች ትላንት ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ተገለጸ።

በመጀመሪያው ዙር ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የማስመለስ ስራ 1500 የሚጠጉ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ከመጀመሪያው ዙር በኋላ የሁለተኛ ዙር ተመላሾች ለተከታታይ ቀናት ሳይንቀሳቀሱ እና ወደ ቀያቸው የማስመለሱ ስራ የተስተጓጎለው ወደ ቀያቸው ከሚመለሱት ተፈናቃዮች መካከል ታጣቂ ሚሊሻዎች በመኖራቸው መሆኑ ተጠቁሟል፤ ከነትጥቃቸው መግባታቸው የሚፈጥረውን ስጋት በመገንዘብ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ለማድረግ በተደረገ ጥረት መሆኑን ተጠቁሟል።

መጉላላቱ የተፈጠረው “ተመላሾችን ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን በማስተባበር ላይ የነበሩ የአማራ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ተፈናቃይ ታጣቂ ሚሊሻዎች እንዳይገቡ በመከላከላቸው መሆኑን” በትግራይ በኩል ተፈናቃዮችን በማስመለስ ረገድ አስተባባሪ የሆኑት ሙላት መኮንን ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

ችግሩ የተፈጠረው በፌደራል መንግስት፣ በትግራይ ሀይሎች እና በአማራ ክልል ባለስልጣናት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ባለመረዳት ነው ሲሉ ገልጸዋል። ስምምነቱ የሚለው ከትግራዩ ጦርነት በፊት በአካባቢው ነዋሪ የነበሩ ታጣቂ ሚሊሻዎች ከነትጥቃቸው እንዲመለሱ ይፈቅዳል ያሉት አስተባባሪው ነገር ግን የአማራ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ሚሊሻዎቹ ከነትጥቃቸው ከገቡ ስጋት ይፈጠራል የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በመጀመሪያው ዙር የጸለምት ወረዳ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው በተመለሱበት ወቅት ያነጋገርናቸው ከትግራይ በኩል ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለማስመለሰ በተዋቀረው ኮሚቴ የማጓጓዣ ጉዳዮች አስተባበሪ የሆኑት ታደለ መንግስቱ ወደ ጸለምት ወረዳ “ከ8ሺ 500 እስከ 10ሺ የሚደርሱ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ” ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

አብዘሃኛዎቹ የክልሉ ተፈናቃዮች ለመንግስት እያቀረቡት ከሚገኙ ጥያቄዎች መካከል የጸጥታ እና ደህንነት ሁኔታው እንደሚያሳስባቸው፣ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መሰረታዊ ነገሮች እንዲሟሉላቸው አለመደረጉ እና በመልሶ መቋቋም ስለሚያጋጥማቸው ተግዳሮት ይገኙበታል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“ወደ ቀያቸው ለሚመለሱ ተፈናቃዮች የአንድ ወር ቀለብ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በመንግስታዊ ባልሆኑ ረድኤት ድርጅቶች እንደተሰጣቸው” አቶ ታደለ አስታውቀዋል።

በአከባቢው የነበሩ የአማራ ክልል መስተዳድር አካላት ተፈናቃዮቹ ከመመለሳቸው ሶስት ቀናት በፊት አከባቢውን ለቀው መውጣታቸውን እና በአሁኑ ሰአት አከባቢው በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መሆኑን አቶ ታደለ ለአዲስ ስታንዳርድ መግለጻቸውን በዘገባው ተካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button