ዕለታዊፍሬዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ኢትዮጵያ ያከናወነችው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አራተኛ እና የመጨረሻ ውሃ መሌት ከግብፅ ተቃውሞ ገጠመው


አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 6/ 2015 ዓ.ም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አራተኛ እና የመጨረሻው የዉሃ ሙሌት መጠነቀቁን ማብሰራቸውን ተከትሎ ግብፅ ድርጊቱን “ህገ-ወጥ” ስትል ተቃወመች፡፡

በሱዳን፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ መካከል በካይሮ ሲደረግ የነበረው ውይይት ያለ አንዳች ውጤት ከተጠናቀቀ ሁለት ሳንት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ትላንት ጳጉሜ 5፣ 2015 የታላቁ ህዳሴ ግድብ አራተኛው እና የመጨረሻው ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

“የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው።” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያበሰሩት ጠ/ ሚንስትሩ በሂደቱ በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎች ማጋጠማቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የወሰደችው የአንድ ወገን ተግባር የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብዕ እና ሱዳን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያደርስ መሆኑን በመግለፅ የውሃ ሙሌቱ ህገ-ወጥ ነው ሲሉ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል፡፡

ሚንስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ይህ የውሃ ሙሌት የታችኛው ተፋሰስ አገራትን ጥቅምና መብት እንዲሁም የውሃ ደኅንነታቸውን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አለመሆኑን በመግለፅ ድርጊቱ በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች የጣሰ ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

ግብጽ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሌት ያከናወነችው ሱዳን፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ በ2007 ዓ.ም. የተፈራረሙትን የመርሆች ስምምነት የሚጥስ ነው ብላለች።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በካይሮ ያለ ስምምነት የተጠናቀቀው ውይይት በመስከረም ወር በአዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ “አራተኛ እና የመጨረሻው” የዉሃ ሙሌት የሚለቀውን በተመለከት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ “አራተኛና የመጨረሻው ሲባል ከዚህ በኋላ የውሃ ሙሌት አይደረግም ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ “አራተኛና የመጨረሻው” የውሃ ሙሌት የተባለው አራቱ ዙሮች ከፍተኛ የውሃ መጠን የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነው ብለዋል። በእነዚህ አራት ዙሮች ግድቡ መያዝ ያለበትን የውሃ መጠን መያዝ መቻሉንም አንስተዋል ።
ይልቁንም ግድቡ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ፣ከፍተኛ የውሃ መጠን ሳያስፈልግ እንደሚከናወን ዶክተር ሃብታሙ አብራርተዋል ። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button