ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራሉ መንግስት ጋር የፖለቲካ ውይይት በአስቸኳይ እንዲጀመር ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18/ 2016 ዓ.ም፡- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በደቡብ አፈሪካ ፕሪቶሪያ ህዳር 2022 በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከፌዴራሉ መንግስት ጋር የፖለቲካ ውይይት በአስቸኳይ እንዲጀመር ጠየቀ፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አማኑኤል አሰፋ ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ እንደገለፁት የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድንን ጨምሮ ለአለም አቀፉ የሰላም አደራዳሪ አጋሮች የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር በተደጋጋሚ ተጠይቆ ምላሽ እየተጠበቀ ነው፡፡

አቶ ዐማኑኤል ጦርነቱ፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ቢቋጭም፣ መንሥኤ የኾኑት ዋነኛ ችግሮች እንዲፈቱ የሚጠበቀው ግን፣ በፖለቲካዊ ውይይት እንደኾነ ሓላፊው ተናግረዋል፡፡ ሰላሙ ዘላቂነት እንዲኖረውና የክልሉ ሕዝብ በርካታ ችግሮቹን ለመፍታት እንዲችል፣ ፖለቲካዊ ውይይቱ ወሳኝ እንደኾነ፣  አክለው አመልክተዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ያጣቸው “የተሟላ በጀት” ድጋፍና ሌሎች ህገ መንግስታዊ መብቶች የሚፈቱት የፖለቲካ ውይይቱን በአስቸኳይ በመጀመር ብቻ ነው ሲሉምአቶ አማኑኤል አክለዋል፡፡ ሰላምን ማስቀጠል እና የትግራይ ህዝብ የገጠሙትን በርካታ ችግሮች እንዲፈታ ማስቻል  አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጠዋል።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር መጠየቁ ይታወሳል፡፡ ፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ሳይሸራረፍ እንዲተገበር የጠየቀው ኮሚቴው በአተገባበሩ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ህወሓት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button