ቢዝነስዜና

ዜና፡ መንግሥት ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከዘጠኝ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22/2016 .ም፡ መንግሥት በ2016 በጀት ዓመት አምስት ወራት ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከዘጠኝ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአምስት ወራት አምስት ሺህ 786 ተሸከርካሪዎች ከድጎማ ተጠቃሚነት መታገዳቸውንም አመላክቷል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎችን በመለየት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ሲሉ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ብሔራዊ የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን መሐመድ መግለጻቸውን የጠቆመው ኢፕድ በ2016 በጀት ዓመት አምስት ወራት ብቻ ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዘጠኝ ነጥብ 82 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በድጎማ ማስተግበሪያ ሥርዓቱ ውስጥ የድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተመዘገቡ 241 ሺህ 035 ጠቅላላ ተሽከርካሪዎች ውስጥ እስከ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 198 ሺህ 771 የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ድጎማ እያገኙ መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል።

በድጎማ ሥርዓቱ ከተመዘገቡት ተሽከርካሪዎች 82 በመቶ የሚሆኑት ተጠቃሚ መሆናቸውን ሃላፊው ገልጸዋል ያለው ዘገባው በበጀት ዓመቱ አምስት ወራት የድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ ተጨማሪ 21 ሺህ 677 ተሽከርካሪዎች መኖራቸውንም ጠቁሟል።

ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተሰጣቸውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉና በሕገወጥ መንገድ ሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ሃላፊው ገልጸው አራት ሺህ 500 ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይሰጡ የተጠቀሙትን ከዘጠኝ ነጥብ 76 ሚሊዮን ብር በላይ የድጎማ ገንዘብ በዕዳ መልኩ መልሰው እንዲከፍሉ መደረጉን አስታውቀዋል።

መንግሥት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች የኑሮ ጫና ለማቃለል የታለመ ዓላማ ያለው የነዳጅ ድጎማ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በ2016 በጀት ዓመት አምስት ወራት ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከዘጠኝ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጓማ ተደርጓል፡፡ አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button