ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የዋስትና መብታቸው የተከበረላቸው የጎጎት ፓርቲ አመራር ከፖሊስ ጣቢያው ግቢ ሳይወጡ ለተጨማሪ ምርመራ በሚል በድጋሚ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17/2016 .ም፡ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ (ጎጎት) የፓርቲው የጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ሳህሌ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር ቢለቀቁም ከፖሊስ ጣቢያው ግቢ ሳይወጡ በድጋሚ በአዲስ አበባ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ በሚል ለእስር መዳረጋቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

አመራሩ ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከስራ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ ላይ እያሉ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወሰዱብኝ ሲል ፓርቲው መግለጹ ይታወሳል።

ፖሊስ አቶ መላኩ ሳህሌ ላይ ክስ ያቀረበው “በአዲስ አበባ ከተማ ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር እና ከጠላት ጋር ማበር” በሚል እንደሆነ ፓርቲው በችሎቱ በመታደም ለማወቅ መቻሉን የገለጸው ጎጎት በመግለጫው ፖሊስ አቶ መላኩ ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት በመፍጠር አዲስ አበባ ላይ ሰዎችን በማደራጀት መንግስት እንዳይረጋጋ  ሰርተዋል ማለቱን ጠቅሷል። ፖሊስ ይግባኝ በጠየቀበት ችሎት በድጋሚ “ከፋኖ ጋርም አብረው ይሰራሉ የሚል ክስ ማቅረቡንም ፓርቲው በላከልን መግለጫ አስታውቋል።

ትላንት ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት የቀረቡት አቶ መላኩ ሳህሌ በአምስት ሺ ብር ዋስትና ውጪ ሆነው ፖሊስ ያቀረበባቸውን ክስ እንዲከታተሉ እንደወሰነላቸው የጠቆመው ፓርቲው ፖሊስ በእለቱ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ እንደጠየቀባቸው እና ይግባኝ የተጠየቀው የአዲስ አበባ ይገባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የፖሊስን ይግባኝ ከመረመረ በኃላ የታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ በማፅናት የፖሊሲ ይግባኝ ውድቅ በማድረግ  ተከሳሽ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው መወሰኑን ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button