ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በሁለት ወራት ገደማ የመጨረሻውን ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም፡- ለሶማሌላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ስምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ መናገራቸው ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ለባሕር ኃይል የጦር ሠፈር ልትከራይ የምትችላቸው ሦስት አማራጭ ቦታዎች መለየታቸውን ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ዶይቼ ቬለ ዘግቧል።

ከአራት ወራት በፊት ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈረመው የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ሰነድ በመጪዎቹ ወራት ወደ ተግባር ይሸጋገራል ብለው የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ዲፕሎማቶች እየተጠባበቁ ይገኛል ተብሏል።

የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን እና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መታጨታቸውን ተናግረዋል።

“ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ነበር” ያሉት ዶክተር ኢሳ ካይድ በረመዳን የጾም ወር ወቅት ሒደቱ ቢቀዛቀዝም በመጪዎቹ ወራት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሥምምነቱን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የመጨረሻውን ሥምምነት ሊፈራረሙ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

“ሁሉም ነገር ሁለቱ ቡድኖች በስምምነቱ ላይ ለመደራደር ሲገናኙ ይወሰናል” ያሉት ዶክተር ኢሳ “የሕግ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች አሉ። በመጪዎቹ ወራት ምን አልባትም በሁለት ወራት ገደማ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ስምምነቱ ከተፈረመ ሶማሌላንድ ዕውቅና ስታገኝ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር የምታቋቁምበትን ወደብ በኪራይ ታገኛለች ያለው ዘገባው ሶማሌላንድ 850 ኪሎ ሜትር ገደማ በሚረዝመው የባሕር ዳርቻ ኢትዮጵያ ልትከራይ የምትችልባቸውን ሦስት ቦታዎች በአማራጭነት መለየታቸውን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኢሳ ካይድ አረጋግጠዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“የለየናቸው የተወሰኑ ቦታዎች አሉ። ከኢትዮጵያ አቻዎቻችን ጋር ከተገናኘን በኋላ አንዱ ይመረጣል” ያሉት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተለዩትን ሦስት ቦታዎች ስሞች ከመናገር ተቆጥበዋል።

“የኪራይ ሥምምነቱን ለመፈራረም ስንስማማ በተመሳሳይ ጠረጴዛ እና በተመሳሳይ ቀን ለሶማሌላንድ ዕውቅና የሚሰጠው የኢትዮጵያ አዋጅ ወዲያው መከተል አለበት” ሲሉ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሒ አብዲ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሥምምት ኢትዮጵያ ለንግድ አገግሎት የሚውል ወደብ (commercial maritime) እንዲኖራት የሚፈቅድ መሆኑን በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደሕንነት አማካሪ የነበሩት ሬድዋን ሑሴይን ተናግረው ነበር።

የሶማሌላንድ የፋይናንስ ሚኒስትር ዶክተር ሳዓድ አሊ ሽሬ ግን የበርበራ ወደብ “የኢትዮጵያን ነጋዴዎች እና መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች እንዲጠቀሙበት ክፍት ይሆናል። ስለዚህ ሌላ ወደብ መገንባት አያስፈልግም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button