ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በኢትዮጵያ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል እንደቀጠለ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሞያዎች ቡድን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8/2016 .ም፡ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ከአንድ አመት በኋላ የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች በኢትዮጵያ (ICHREE) ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ አሁንም የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል እንደቀጠለ ነው ሲል ገልጿል። በሀገሪቱ ሰላም ሰፍኗል ለማለት አስቸጋሪ ነው ሲል ቡድኑ በሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

21 ገጽ ባለው ሪፖርቱ እንደተገለጸው በጦርነቱ የተሳተፉ ሁሉም አካላት ጦርነቱ ማግስት ጀምሮ ግፍ ፈጽመዋል ብሏል። ከተዘረዘሩት ግፎች መካከልም ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማስራብ፣ የትምህርት እና የጤና ተቋማት ውድመት፣ ማፈናቀል እና የዘፈቀደ እስር  ይገኙበታል።

የሰላም ስምምነቱ የጦር መሳሪያ ድምጾችን ዝም ቢያሰኝም በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በተለይም በትግራይ ያለውን ግጭት አልፈታም፣ ሙሉ ሰላም አላመጣም ሲሉ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሞሃመድ ቻንዲ ኦትማን ተናግረዋል። አሁንም በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚባል መልኩ ሀይል የተሞሉ ግጭቶች ተበራክተዋል፣ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልል በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ከፍተኛ በደሎች እየጨመሩ ነው ብለዋል።

በኮሚሽኑ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የኤርትራ እና አማራ ታጣቂዎች በትግራይ የሚፈጽሙት ግፍ እንደቀጠለ ነው፤ የተደራጀ አስገድዶ መድፈር እና በሴቶእ ላይ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃቶች መፈጸማቸውን አመላክቷል።

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ካጋለጣቸው ጉዳዮች መካከልም በኦሮምያ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በክልሉ ንጹሃን ላይ እስራት፣ ማጎር እና ቶርቸር ፈጽመዋል የሚለው ይገኝበታል። በአማራ ክልል የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲሀ ደግሞ በርካታ ግፎች በንጹሃን ላይ መፈጸሙን አስታውቋል። ቢያንስ አንድ የድሮን ጥቃት በፌደራል መንግስቱ ተፈጽሟል ብሏል።

የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በትግራይ ሴቶች ላይ የሚፈጽሙትን አስገድዶ መድፈር እና ወሲባዊ ጥቃት አሳሳቢ ነው ያሉት ኮሚሽነር ራድሂካ ኩማራስዋሚ የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በኢትዮጵያ ግዛት ለይ እንዲቆዩ መደረጉ የፌደራል መንግስቱ ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ከለላ ከመስጠት ባለፈ ግፉን እንደመደገፍ እና እንደመታገስ የሚያስቆጥርለት ነው ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ መንግስት የጥቃቱ አድራሾቸ በአግባቡ እንዲመረመሩ ወይንም ተጠያቂ እንዲሆኑ አለማድረጉን የተቸው ኮሚሽኑ መንግስት ይልቁንም ያተኮረው ለተጠቂዎች በአግባቡ ቦታ ያልሰጠ የተዛባ የሽግግር ፍትህ ምክክር ላይ ብቻ ነው በሏል። አለም አቀፍ ምርመራ እንዳይካሄድ ሆን ብሎ እንቅፋት እየፈጠረ ነው ሲል ኮንኗል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button