ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ለሁለት ቀናት በካይሮ ጉብኝት ያደረጉት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ኳታር ዶሃ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10/2016 ዓ.ም፡- በሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቀናት በግብጽ ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሀሙድ ወደ ኳታር ማቅናታቸው ተገለጸ።

በኳታር ይፋዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸውን የተገለጸው ፕሬዝዳንቱ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስለጣናት በሀገራቱ ግንኙነት እንደሚወያዩ እና በተለይም በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል ስለተደረሰው ስምምነት እንደሚመክሩ ተጠቁሟል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ማህሙድ ከኳታር ባለስለጣናት ጋር በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ተጠቁሟል።  

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንትን ሀሰን ሸክ መሀሙድን በቤተመንግስታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በኢትዮጵያ ላይ የቀጥታ ዛቻ መሰንዘራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የአልሲሲን ዛቻ ተከትሎ የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሶማሊላንድ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት በጽኑ እንደምትቃወም አስታውቋል፤ ግብፅ ግጭት የማስቆም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን በቀውስ በመናጥ ላይ ላሉት አጎራባቾቿ ሱዳን ሊቢያ እና ጋዛ ብታደርግ ይበረታታል ሲል ገልጿል።

ማንኛውም በቀጠናው ፍላጎት ያለው አካል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥቅሙን ለማስከበር ጥረት ማድረግ ላይ ብቻ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ሲል ምክሩን ሰንዝሯል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button