ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አልሲሲ በኢትዮጵያ ላይ የቀጥታ ዛቻ ሰነዘሩ፣ ለሱማሊያ ባስቸጋሪ ጊዜዎቿ የደረሰችላት ኢትዮጵያ ናት ሲሉ ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13/2016 ዓ.ም፡- የሶማሊያውን ፕሬዝዳንትን ሀሰን ሸክ መሀሙድን በቤተመንግስታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በኢትዮጵያ ላይ የቀጥታ ዛቻ ሰነዘሩ።

“ለኢትዮጵያ ያለኝ መልዕክት የሶማሊያን ቅንጣት መሬት ለመቆጣጠር መሞከር ማንም የሚቀበለው አለመሆኑን ነው” ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል በዘገባው አስታውቋል።

በተጨማሪም የዜና አውታሩ በዘገባው አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር በቤተመንግስታቸው በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ግብጽን አትፈትኗት፣ ወንድሞቿንም እንዲሁ፤ በተለይም ሶማሊያ ጣልቃ እንድንገባ ከጠየቀችን ወደ ኋላ አንልም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል ብሏል።

ሀገራቸው ሶማሊያን ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ ያስታወቁት አልሲሲ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተቀባይነት የለውም ሲሉ ገልጸዋል። በሶማሊያ ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንዲፈጸምባት አንፈቅድም፣ የሶማሊያ ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነት ሊጠበቅ ይገባዋል ብለዋል።

በተያያዘ ዜና የአልሲሲን መግለጫ ተከትሎ የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን በኤክስ የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለሱማሊያ ባስቸጋሪ ጊዜዎቿ ምንም ድጋፍ ያላደረጉላት ነገር ግን አሁን የልብ ወዳጅ ሁነው ለመቅረብ የሚሞከሩ አካላት እውነተኛ መነሻቸው “ለኢትዮጵያ ያላቸው የጠላትነት ስሜት ነው” ሲሉ ተችተዋል፤ ዋነኛ አጀንዳቸው በቀጠናቅው ሰላም እና ደህንነት ማስፈን ሳይሆን አለመግባባት እና ቀውስ መፍጠር ነው ሲሉ ኮንነዋል።

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም እና ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በውድ ልጆቿ ደም እና ላብ በግልፅ አሳይታለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው ስምምነት የባህር በር የሚያስገኝላት የትብብርና አጋርነት ስምምነት እንጂ “ግዛት መጠቅለል” ወይም “ሉዓላዊነትን በሌላ አገር ግዛት ላይ ማወጅ አይደለም” ሲሉ አስታውቀዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button