ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በካይሮ እየተካሄደ ያለው የሶስትዮሽ ድርድር በስምምነት ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 22/2015 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር ከተቋረጠ ሁለት አመት ከአምስት ወር ሁኖታል፤ ይሁን እንጂ ትላንት ነሃሴ 21 ቀን 2015 ዓ.ም የሶስትዮሽ ድርድሩ በካይሮ እንደገና መጀመሩን ከሁሉም ቀድመው የግብጽ መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሳዊላም አብስረዋል። አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ጉዳዩን ተቀባብለው እያሰራጩት ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የሶስትዮሽ ድርድሩ በካይሮ መጀመሩን አብስሮ የሶስትዮሽ ድርድሩ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ ሲደረግ መቆየቱን እና ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ከዛ ወዲህ ድርድሩ ሳይካሄድ መቆየቱን ጠቁሟል።

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚካሄዱ ድርድሮች በቅርቡ በስምምነት እንደሚቋጩ ያላቸውን ተስፋ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሸክ ሻህቡት ናህያን አል ናህያን በቅርቡ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል። ስምምነቱ የሶስቱን ሀገራት ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ይሆናል የሚል እምነታቸውንም አጋርተዋል።

ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሚል አቋም በተደጋጋሚ ስታሰማ የነበረችው ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ብቻ እንዲካሄድ ስትወተውት ሰንብታለች። በትላንትናው ዕለት የመንግስት የኪሙዩኒኬሽን አገልግሎት በይፋዊ የፌስቡክ ትስስሩ ገጽ ላይ ያሰፈረው መረጃ ግን በተቃራኒው ነው፤ በተባበሩት አረብ ኤሚሬት አሸማጋይነት ድርድሩ ሲካሄድ እንደነበር ተጠቁሟል።

የግብጹ የመስኖ ሚኒስትሩ ሃኒ ሳዊላም የሶስትዮሽ ድርድሩ መጀመሩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ግብጽ በህዳሴ ግድብ አሞላል እና አስተዳደር ዙሪያ አስገዳጅ ህጋዊ ውል መፈራረም እንደምትፈልግ መግለጻቸውን አሶሴትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ባሰራጨው ዘገባ አስታውቋል። በተጨማሪም አጨቃጫቂ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ቴክኒካዊ እና ህጋዊ መፍትሔዎች አሉ ሲሉ መግለጻቸውንም የዜና አውታሩ በዘገባው አካቷል፤ ሚኒስትሩ መፍትሔዎቹን ባይጠቁሙም።

ዋናው የሶስትዮሽ ድርድሩን ሲያጓትት የነበረው ጉዳይ በታችኛው ተፋሰሱ ሀገራት የተራዘመ ድርቅ ቢከሰት ምን ያክል ውሃ ይለቀቃል የሚለው እና ሶስቱ ሀገራት ባይስማሙ በምን መንገድ ልዩነቶች ይፈታሉ የሚለው መሆኑን የጠቆመው የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ኢትዮጵያ ምንም አይነት አስገዳጅ ውል አልፈርምም ስትል መቆየቷን አውስቷል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው የተቋረጠው ድርድር የተጀመረው ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በግብፅ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት ነው። ነገር ግን ድርድሩ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እና የወደፊት የመልማት መብት ባስከበረ መልኩ ለማካሄድም አስፈላጊው ዝግጅት ተከናውኗል ከማለት ውጪ ተጨማሪ መረጃ አላቀረበም።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ረቂቅ ስምምነቱ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ድርድር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

በሶስትዮሽ ድርድሩ መጀመር ዙሪያ ዘገባ ይዞ የወጣው አረቢ 21 የአረብኛ ድረገጽ ላለፉት አስር አመታት ከአባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ የተናጠል እርምጃ ይቁም፣ አስገዳጅ ውል መፈራረም ይገባናል የሚሉ መሰል ጥያቄዎች እና አቋሞች በግብጽ በኩል ሲሰሙ እንደነበር አውስቶ  ከወራት በፊት የግብጹ ፕሬዝዳን ከአብይ አህመድ ጋር በግብጽ በነበራቸው ውይይት በአስገዳጅ ውሉ ዙሪያ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ እንዳልቀረ ጠቁሟል።

ከሚያዚያ 2013 ዓ.ም ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ በመካሄድ ላይ ለሚገኘው የሶስትዮሽ ድርድር መሰረት የጣለው በያዝነው አመት ሰኔ ወር ላይ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በግብጽ ተገኝተው ከአልሲሲ ጋር መምከራቸው መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ አረቢ 21 ድረገጽ ያነጋገራቸው የውሃ እና ግድብ ባለሞያው ዶ/ር ሙሃመድ ሃፋዝ አል ሲሊ ለኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር በገድቡ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት ለማቻቸል የገቡላቸው ቃል በመኖሩ ሳቢያ ነው የሚል እምነት አንዳላቸው ጠቁመዋል። የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ከግብጽ እንደተመለሱ ወዲያውኑ የሰጡት መግለጫ እጅግ መደሰታቸውን የሚጠቁም፣ ትልቅ እፎይታ እንደተሰማቸው እና ከዚህ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ልዩነት እንዳልነበር ያክል በፈንጠዝያ የተሞላ ነው ሲሉ ገልጸው ይህም ሊሆን የሚችለው ግብጽ ለኢትዮጵያ ከአባይ ውሃ የመጠቀም ድርሻ አንዲኖራት በግብጽ በኩል በይፋ ስለተገለጸላት ቢሆን ነው ሲሉ ገልጸዋል። ታሪካዊ መብት ያለኝ ብቸኛዋ እኔ ነኝ ከሚለው አቋሟ ማፈግፈጓን እና ወደ የመሃል መፍትሄ አማራጭ መምጣቷን በመጠቆም።

ዋናው እና ቁልፉ ጉዳይ በትራምፕ አደራዳሪነት ተካሮ የነበረው የውሃ አለቃቀቅ መፍትሔ ያገኘ ይመስላል ያሉት ባለሞያው ሃፋዝ በትራምፕ አደራዳሪነት በነበረው ውይይት ኢትዮጵያ 31 ቢሊየን ኪዩቢክ ውሃ ለመልቀቅ ሃሳብ ማቅረቧን እና ይህመ በካይሮ በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን እና የሚለቀቀቅ የውሃ መጠን 40 ቢሊየን ይድረስ መባሉን አውስተዋል። አሁን ይህ የተካረረ ልዩነት የተፈታ ይመስላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ባለሞያው በተጨማሪም ዩየተባበሩት አረብ ኤሚሬት ሁለቱንም በማደራደር ዙሪያ ትልቅ ሚና መጫወቷን ጠቁመው የግብጽን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ኢትዮጵያ ከዘጠኝ እስከ አስራ ስድስት ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ባለመብት እንደተደረች እና ኢትዮጵያ ደግሞ በህዳሴ ግድብ የምትይዘውን ውሃ በሚያሳንስ መልኩ የግድቡ መሃል ከፍታ ከ625 ወደ 620 ዝቅ እንዲል መደረጉን በአብነት አስቀምጠዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button