ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በትግራይ የሚገኘው ዓዴፓ የፌዴራል መንግስት “ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ የያዘውን አቋም” እቃወማለው አለ፤ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ አንዲተገበር ጥሪ አቅረበ 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/ 2016 ዓ ም፦ በትግራይ የሚገኘው ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ)፣ በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ስራ የሚገኙ ምዕራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ አከባቢዎች ላይ የፌዴራል መንግስት ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ የያዘው አቋም “ህገ መንግስታዊ ያልሆነና የነዋሪ ህዝብ ፍላጎት ያላገናዘበ አቋም” ሰለሆነ በአስቸኳይ እንዲስተካከል ሲል ጠየቀ፡፡ 

ድርጅቱ ከትላንት ብስቲያ ባወጣው መግለጫ በፕሪቶርያው ሰላም ስምምነቱ መሰረት ተግባራዊ ያልሆኑ ወሳኝ ጉዳዮች መተገበር አስፍላጊ መሆኑን  አክሎ ጠቅሷል፡፡

ዓዴፓ አንድ አመት ባስቆጠረው ሰምምነቱ ተግባራዊ ካለተድርጉት መካከል አንዱ የኤርትራ ሰራዊት  ከኢሮብ፣ ዛላንበሳ፣ እገላ፣ ባድመ ፣ ዓዲ ጉሹ እና ከሌሎች የትግራይ ግዛቶች አለመውጣቱ መሆኑን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም የአማራ ታጣቂዎች ከምዕራብ ትግራይና ከደቡብ ትግራይ አለመውጣታቸው ፓርቲው አስታውቋል፡፡

ሱዳን ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ያሉ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ አከባቢያቸው አለመመለሳቸው፤ በትግራይ ክልል ሲሰጥ የነበረው የሰብአዊ እርዳታ ለበርካታ ወራት በመቋረጡ ቡዙ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆናቸው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ምሆኑን ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ፓረቲው የኤርትራ ሰራዊት፣ ፋኖ እና የአማራ ታጣቂዎች የትግራይ መሬት ሙሉ ለሙሉ ለቆ እንዲወጡ፣ በሱዳን ያሉ ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች በአስቸኳይ ወደ አከባቢያቸው እንዲመለሱና በረሃብ እየሞቱ ለሚገኙ ትግራይ ተወላጆች በአሰቸኳይ እርዳታ እንዲደርሰላቸው ጠይቋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button