ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አሁንም ለድርድር ዝግጁ ነኝ ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15/2016 ዓ.ም፡- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በቃል አቀባዩ ኦዳ ተርቢ በኩል አሁንም ለማንኛው የሰላም ድርድር ዝግጁ እና ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል። ለሰላም ድርድር ምንግዜም በራችን ክፍት ነው ብሏል።

የቃል አቀባዩ መግለጫ የወጣው በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) መካከል በታንዛንያ ዳሬሰላም ሲካሄደ የቆየው የሰላም ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ለድርድሩ አለመሳካት መንግስት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በበኩሉ ድርድሩ ያልተሳካው በመንግስት ዳተኝነት ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል።

ቃል አቀባዩ በማህበራዊ የትስስር ኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የዳሬሰላሙ የሰላም ድርድር ያልተሳካው መንግስት በዋነኛ የክልሉ ችግሮች ለመደራደር ፍላጎት ከማሳየት ይልቅ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችን ስልጣን እና ገንዘብ በመስጠት ለመደለል መሞከርን ምርጫው አድርጓል ሲሉ ተችተዋል።

በተጨማሪም ቃል አቀባዩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግጭቱን ለማብረድ እና ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ ሁኖ እየተነጋገረ በነበረበት ወቅት መንግስት የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ያደርግ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

መንግስት ድርድሩ አለመሳካቱን ባስታወቀበት መግለጫው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) በዳሬሰላሙ ድርድር ይዟቸው ይቀርባሉ ብሎ ጠብቆ የነበረው ነጥቦች ሀገሪቱ ከደረሰችበት ምዕራፍ ጋር የተጣጣሙ ይሆናሉ የሚል እንደነበር ገልጾ ነገር ግን በዳሬሰላሙ ድርድር ቡድኑ ይዞት የቀረበው የድርድር ነጥብ “መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ” የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ነው ሲል መተቸቱ ይታወሳል።

መንግስት በመግለጫው የሽብር ቡድኑ ሲል የጠራው በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል ብሏል። በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል ሲል ቡድኑን ኮንኗል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button