ዜናፖለቲካቢዝነስ

ዜና፡ ፌደራል ፖሊስ ከቻይና ማኅበረሰብ የኢንቨስትመንት አባላት ጋር በሚያጋጥማቸው የፀጥታና ደኅንነት ስጋት ዙሪያ መምከሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ የተሰማሩ የቻይና ባለሀብቶች በሚያጋጥማቸው የፀጥታና የደኅንነት ስጋት ዙሪያ ፌደራል ፖሊስ ከቻይና ማኅበረሰብ የኢንቨስትመንት አባላት ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት መምከሩን አስታወቀ።

የምክክሩ ዓላማ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በኢትዮጵያ የቻይና ኢንቨስትመንቶች ላይ የፀጥታ ጥበቃ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን መንገድ ለመዳሰስ እንደሆነ እና የቻይና ባለሀብቶች ያጋጠማቸውን የፀጥታና የደኅንነት ስጋት ላይ በመምከር የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ባደረጉት የመክፍቻ ንግግር መግለጻቸው ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ እያለ የመጣ በመሆኑ ውይይታችን በሁለቱ ሀገራት መሪዎች የተደረሱትን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉም ኮሚሽነሩ መናገራቸውን የፌደራል ፖሊስ በይፋዊ የፌስቡክ የማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ሚስተር ዛሆ ዚ ዩሀን በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲን፣ የቻይና ዜጎችን እና የቻይና ኢንተርፕራይዞችን ደህንነት ለመጠበቅ ላደረጉት ጥረት ከፍተኛ ምስጋና ማቅረባቸውን መረጃው አካቷል።

አምባሳደሩ በቻይና ዜጎችና ኢንተርፕራይዞች ላይ ያነጣጠሩ ወንጀሎችን አውግዘው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥንቃቄና ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አድንቀዋል ብሏል የፌደራል ፖሊስ መረጃ።

በኢትዮጵያ የቻይና የንግድ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ሚስተር ዋንግ ሂ ቻይና በርካታ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባትና የስራ ዕድል በመፍጠር የኢትዮጵያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አፋጥናለች ማለታቸውንም አስታውቋል።

ለዚህም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጥበቃ ኃይሎችን ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በማሰማራት፣ በማስተባበር፣ ጥበቃን በማጠናከርና በወንጀለኞች ላይ ጠንካራ እርምጃዎችን በመውሰድ የቻይና ኢንተርፕራይዞችን የምርትና የአሰራር ቅደም ተከተል በብቃት በመጠበቅ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል ሲሉ ዋና ፀሃፊው ተናግረዋል ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሰላምና ደህንነት ከምንም ነገር በላይ ልንጠብቀውና ልናረጋግጠው ይገባል ሲሉ ዋና ፀሃፊው አሳስበዋል ያለው መረጃው አያይዘውም ለኢንቨስትመንት እንቅፋት ለሆኑ አንዳንድ የፀጥታ ችግሮች መፍትሄ ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦችን ማቅረባቸውን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ሚስተር ዛሆ ዚ ዩሀን የተመራውን ልዑክ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ሲደርስ በፖሊስ ማርቺንግ ባንድ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button