ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ መንግስት በትግራይ ከተካሄደው ጦርነት ጋር የተገናኙ “ወንጀለኞችን” ተጠያቂ አድርጊያለሁ፣ “ተገቢውን እርምጃም” ወስጃለሁ ሲል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23/2016 ዓ.ም፡- ህወሓት ለ41 ቀናት አካሄድኩት ባለው ግምገማና ውይይት ማጠናቀቂያ ዙሪያ ትላንት ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር መጠየቁን ተከትሎ የፌደራል መንግስት በኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ በኩል ምላሽ ስጥቷል።

“በህወሓት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ” የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን የፌዴራል መንግሥት በአንክሮ ተመልክቶታል ያለው የመንግስት መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ከአቋም ባሻገር ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርጓል ብሏል።

መንግስት ለፕሪቶርያው ስምምነት ትግበራ የወሰዳቸውን እርምጃዎች እና ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎችንም በዝርዝር በመግለጫው ጠቅሷል።

“ከሰሜኑ ጦርነት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥቱ ተገቢውንርምጃ በእርሱ በኩል ወስዷል ያለው መግለጫው  ተጠያቂ መሆን ያለባቸውንም ተጠያቂ አድርጓል ብሏል።”

ሌሎች ሥራዎችንም ለማከናወን እንዲቻል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዐዋጅ ረቂቅ ዝግጅት ማጠናቀቁንም አስታውቋል።

ይህ ሂደት እንዲሳካም እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ የትግራይ ክልልም ተገቢው ሚና እንዲጫወት ይጠበቃል ሲል አሳስቧል፡፡

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ37 ቢልዮን ብር በላይ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ክልል ድጋፍ” ማድረጉንም በመግለጫው አመላክቷል፡፡ በተመደበው በጀትና ድጋፍ የክልሉ ዕቅድ ተግባራዊ ተደርጎ ለሕዝብ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣም ይጠብቃል ብሏል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በሕወሐት በኩል ተሰልፈው የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ አለባቸው ያለው መግለጫው ለዚህም የሚረዳ የተሐድሶ ኮሚሽን የፌዴራሉ መንግሥት ማቋቋሙን፣ የሚጠበቅበትን የሰው ኃይልና በጀትም መመደቡን ገልጿል፡፡

ለትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል የፌዴራሉ መንግሥት በርካታ ተግባራት ከሚገባው ባሻገር ተጉዞ አከናውኗል ያለው መግለጫው ለክልሉ ሕዝብ መደረግ ያለባቸው ድጋፎችንም በራሱ ዐቅምም ሆነ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለማከናወን ምንጊዜም ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡

ለትግራይና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚያደርጉ፤ የክልሉን ዕቅዶች ወደ መሬት በሚያወርዱ፤ የክልሉን ሕዝብ ችግሮች በተጨባጭ ለመፍታት በሚያስችሉ ገቢራዊ ነገሮች ላይ ማተኮር አማራጭ የሌለው ነው ብሎ የፌዴራሉ መንግሥት ያምናል ሲል በመግለጫው አካቷል፡፡

የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ለፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት መፈጸም ሙሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ መኖሪያቸው ለመመለስ እንዲቻል የፌዴራሉ መንግሥት የሚመለከታቸውን አካላት አቀናጅቶ ሥራ መጀመሩን ጠቁሞ በአንዳንድ አካባቢዎችም ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ አድርጊያለሁ ብሏል፡፡

የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናንት ከሚመለከታቸው ከአማራና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር አውስቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button