ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ አቋርጣ የነበረውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች ብቻ በማቅረብ እንደምትጀምር አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25/2016 .ም፡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ከአራት ወራት በኋላ እንደሚጀምር ማስታወቁን አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል አስታውቋል። የእርዳታ እህል አቅርቦቱ የሚጀምረው በሀገሪቱ ተጠልለው ለሚገኙ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች ብቻ መሆኑንንም የዜና አውታሩ ጠቁሟል።

የረድኤት ተቋሙ የእርዳታ አቅርቦቱን ለማስጀመር ውሳኔ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ተጠልለው ለሚገኙ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች ላይ ለሚካሄደው የእርዳታ ማጓጓዝ፣ ማከማቸት እና ማከፋፈል ዙሪያ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደማይኖረው ስምምነት ላት በመደረሱ መሆኑን የዩኤስኤድ ቃል አቀባይ እንደገለጹለት የዜና አውታሩ በዘገባው አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ለሚገኙ አንድ ሚሊየን ለሚሆኑ ከሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሌሎች አከባቢዎች ለመጡ ስደተኞች የሚውል ክምችት እንደሚኖር ተጠቁሟል።

የረድኤት ተቋሙ በሀገሪቱ በድርቅ እና ከቀያቸው በመፈናቀላቸው ሳቢያ የምግብ እርዳታ ለሚጠባበቁ 20 ሚሊየን ለሚበልጡ ዜጎች የእርዳታ አቅርቦት እንደማይጀምር ተገልጿል።

በኢትዮጵ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጎጂዎች ተብሎ የሚቀርብ እርዳታ ላልታለመለት አላማ እየዋለ መሆኑ በመረጋገጡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን የእርዳታ አቅርቦት ማቋረጡ ይታወሳል።  

የምግብ እርዳታ የማቋረጡ ውሳኔ እጅግ አዳጋች እና አስቸጋሪ ቢሆንም ውሳኔውን ለማሳለፍ ተገደናል ሲል ረድኤት ድርጅቱ ቃል አቀባይ በአሜሪካን ኤምባሲ በኩል ከአራት ወራት በፊት ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው የኢሜይል መልዕክት ያስታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያ የእርዳታ ተደራሺነት አሰራር ስርአት ዙሪያ ተገቢ የሆነ ማሻሻያ እስኪደረግ ድረስ በውሳኔው እንደሚጸና ማመላከቱን በዘገባችን ተመላክቷል።

የእርዳታ አቅውርቦቱን በኢትዮጵያ ለማስቀጠል ከመንግስት ጋር መሻሻል ስለሚገባቸው አሳራሮች እና ጉዳዮች ላይ እየተነጋገርን ነው ሲሉ ቃል አቀባዩ መናገራቸውን ያስታወቀው የዜና አውታሩ ዘገባ አሰራሮቹ አለም አቀፍ አሰራርን የተከተሉ እንዲሆኑ እንሻለን ማለታቸውን አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

እንደ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ሁሉ የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሲያቀርብ የነበረውን እርዳታ በተለያዩ መንገዶች ላልታለመለት አላማ እየዋለ ነው በሚል ላልተወሰ ግዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማቆሙን ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button