ዜናጤና

ዜና: በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ ተደረገ

ዜና: በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፡- በቀጣይ 4 አመታት የሚተገበር አዲስ ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂክ እቅድ (HIV/AIDS National Strategic Plan 2023/24-2026/7) ይፋ መደረጉ ተገለጸ።

ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የስትራቴጂክ እቅዱ ዋና ግብ ለቀጣይ አራት አመታት የኤችአይቪ ስርጭትን ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ ያለመ ነው።

በተጨማሪም አዳዲስ በኤችአይቪ የመያዝ እና የሞት ምጣኔ በመቀነስ በአገር አቀፍ ደረጃ በ10,000 ሕዝብ ከ1 በታች ለማድረስ መሆኑን አመላክቷል።

በስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ሂደቱ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ አማካሪዎች እንደተሳተፉበት ጠቁሟል።

በስትራቴጂክ እቅዱ ዝግጅት ወቅት የተለያዩ መረጃዎች የተሰበሰቡ ሲሆን፤ የኤችአይቪ ኤፒዲሚዮሎጂ እና የፕሮግራም አፈፃፀም ሰነድ ግምገማ፣ በመስክ ጉብኝት የተሰበሰቡ መረጃዎች አንደግብአትነትም ለመጠቀም መቻሉን  የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠርያ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ መግለጻቸውን አስታውቋል።

የስትራቴጅክ እቅዱ ተዘጋጅቶ መጠናቀቅን ተከትሎ በኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ ላይ የተሰማሩ ሁሉም ፈጻሚዎችና ባለድርሻ አካላት የወደፊት የስራ እቅድ በጋራ ማዕቀፍ ላይ የተገነባ እንዲሆን ለማድረግ ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን በየደረጃው ስትራቴጂክ እቅዱን የማስተዋወቅ ስራ መሰራቱም ተጠቁሟል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተጨማሪም በሰባት ዙር ለሁሉም ክልሎች/ከተማ አስተዳደር እና ለ300 ከፍተኛ የኤችአይቪ ስርጭት ምጣኔ ከተመዘገበባቸው ወረዳዎች ለተውጣጡ የኤችአይቪ ፕሮግራም ባለሙያዎች በስትራቴጂክ እቅዱ ላይ ከክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ጥልቅ የሆነ የስትራቴጂክ እቅድ የማስተዋወቅ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button