ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአማራ ክልል በሽዋ ሮቢት ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ጥቃቱ ተከትሎ በአካባቢው የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16/ 2016 ዓ/ም፡- ትላንት የካቲት 15/ 2016 ከአዲስ አበባ ወደ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከሚሴ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበስሩ ስምንት ሰዎች፤ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች ተገደሉ።

ጥቃቱን ተከትሎ የመዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው አውራ ጎዳና መንገድ (አስፈልት) ላይ የሰውና የንብረት እንቅስቃሴ እገዳ ጥሏል።

ክስተቱን ለአዲስ ስታንዳርድ ያሳወቀ ምንጫችን እንደገለጸው ከተገደሉት ስምንት ሰዎች ውስጥ አምስቱ መምህራን ሲሆን የተቀሩት ሶስቱ ደግሞ ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ሴት የቤት ሰራተኞች ነበሩ።

ምንጩ አክሎ እንደገለጸው ሰዎቹ እየተጓዙበት የነበረውን ተሽከርካሪ ታጣቆዎቹ በማስቆም “መታወቂያቸውን በማየት የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን ካረጋጋጡ በኋላ ገደሏቸው” ሲል ገልጿል።

ለአዲስ ስታንዳርድ ከተላከው የተንቀሳቃሽ ምስል( ቪዲዮ) መረዳት እንደተቻለው፤ ቶሎሳ ኩሩ፣ ኤፍሬም እንዳለው፣ ኢድሪስ ሞሀመድ እና ገመቹ ካሳሁን የሚባሉ ገለሰቦች ከተገደሉስ ሰዎች መካከል ናቸው። 

ግድያውን ተከትሎ የሸዋ መዓከላዊ ኮ/ፖስት ዛሬ የካቲት 16/ 2016 ባውወጣው መግለጫ “ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው አውራ ጎዳና  የአስፋልት መንገድ ላይ በንፁሀን መንገደኞች ላይ ግድያ፣ እገታ፣ ዘረፋና መሰል አሰቃቂ ወንጀሎች በፅንፈኞች እየተፈፀመ ይገኛል” ሲል ገልጿል።  

ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጸው ኮማንድ ፖስቱ “የንፁሀንን ህይወትና ንብረት ከአደጋ ለመታደግ” ሲባል ከነገ የ ካቲት 16/2016 ንጋት 12:00 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በዋናው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው አውራ ጎዳና መንገድ/አስፈልት ላይ የሰውና የንብረት እንቅስቃሴ አገዳ ተጥሏል ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ስለሆነም ሁሉም የ መንግስት የ ፀጥታ ሀይሎችና የ መንግስት ተቋማት እገዳውን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ፣ ዜጓች መንገድ ላይ እንዳይጉላሉ ከመነሻ መረጃ እንዲሰጣቸው፣ የ ትራፊክና የ መንገድ ትራንስፖርት ተቋማት /መነሀሪያዎች፣ ሚዲያዎች ወዘተ  ትብብር እንዲያደርጉ የ መዓካላዊ ሸዋ ኮ/ፖስት አሳስቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button