ዜናጤና

ዜና፡ በአዲስ አበባ የተገነባው የአልትራሳንውንድ ህክምና መሳሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4/2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ በሚገኘው ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው የአልትራሳውንድ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ትላንት የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ተጠቆመ።

ኤልስሜድ ሶሊሽንስ እና ሲመንስ የተሰኙ ኩባንያዎች በጋራ ያስገነቡት የአልትራሳውንድ መገጣጠሚያ ፋብሪካው የተለያዩ ዓይነት ህመሞችን መመርመር የሚያስችል መሳሪያዎች የሚገጣጠሙበት መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ያጋራው መረጃ ያሳያል።

የፋብሪካው ወደ ሥራ መግባት ከኢትዮጵያም ባለፈ በአፍሪካ በላቀ ቴክኖሎጂ ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ መናገራቸውን የገለጸው መረጃው ፋብሪካው በተለይም በህክምና ዘርፍ ለተሰማሩ ቴክኒሻኖች፣ መሃንዲሶችና ደጋፊ ባለሙያዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር በኩል ወሳኝ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ነው ማለታቸውንም አስታውቋል።

የኤልስሜድ ሶሉሽን ኩባንያ ፕሬዝዳንት ሮኔን ባሁር በበኩላቸው ከረጅም ዓመታት ዝግጅት በኋላ የፋብሪካው እውን መሆኑን እና ለፋብሪካው እውን መሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ትልቁን ድርሻ የሚወስድ ነው ሲሉ አድናቆታቸውን መግለጻቸው ያመላከተው መረጃው በኢትዮጵያ ያደረግነው ኢንቨስትመንት ሌሎች ኩባንያዎችን ኢትዮጵያን ተመራጭ መዳረሻ እንዲያደርጉ በር የሚከፍት ነው ማለታቸውን አመላክቷለ።

የኤልስሜድ የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ኃይሉ በበኩላቸው በፋብሪካው የሚመረቱ መሳሪያዎች በኢትዮጵያ የተሰራ /Made in Ethiopia/ መለያ ብራንድ የሚጻፍባቸው በመሆኑ ለኢትዮጵያ ኩራት ነው ሲሉ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ፣ የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የጀርመንና የእስራኤል አምባሳደሮችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውም ተካቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button