ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በኢትዮጵያ ለተረጂዎች የማከፋፍለው የምግብ እርዳታ በዲጂታል ሲስተም የታገዘ መሆኑ ውጤት እያስገኘ ነው – አለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27/2016 ዓ.ም፡- የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ዲጂታል ሲስተም በመጠቀም በረሃብ ለተጠቁ ሰዎች የምግብ እርዳታ ለማቅረብ የማደርገው የከትትል እና ስርጭት ዘዴ ውጤት እያመጣ ነው ሲል ገለጸ።

በኢትዮጵያ የእርዳታ አቅርቦት ለታለመለት አላማ እየዋለ ባለመሆኑ ምክንያት እና ለተጎጂዎች እንዲዳረስ ለማስቻል በማለም አዲስ አሰራርን እንዲከተል መገደዱን ያመላከተው ፕሮግራሙ የተራቀቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የእርዳታ እህሉ ለተጎጂዎች መዳረሱን ለመከታተል እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። ውጤት አስገኝቶልኛልም ሲል ማሳያዎችን በማቅረብ በድረገጹ አስነብቧል።

በድጋሚ የእርዳታ አቅርቦት ከጀመረበት ከታህሳስ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ለሚሆኑ ተጎጂዎች የምግብ እርዳታ ማከፋፈሉን አስታውቋል።

በቀጣይ ሳምንታትም ወሳኝ የሆነ የምግብ እርዳታ አቅርቦት ለማከፋፈል እየተጣደፍኩ ነው ሲል ገልጿል፤ አብዘሃኛዎቹ ተረጂዎች፣ ሁለት ሚሊየን የሚሆኑት የትግራይ መሆናቸውን ጠቁሟል።

የመንግስታቱ ድርጅት የምግብ ፕሮግራም በትግራይ የእርዳታ እህል ከሚያከፋፍላቸው መካከል ግማሽ የሚሆኑት በመንግስት ብሔራዊ የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም የታቀፉ መሆናቸውንም አመላክቷል።

የአለም የምግብ ፕሮግራም የተረጂዎችን ልየታ የሚያከናውነው ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር መሆኑን አስታውቋል፣ በየአከባቢው ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እና ከየአከባቢዎቹ የመንግስት አስተዳደሮች ጋር በመተባበር መሆኑን አመላክቷል፣ የሂደቱ ዲዛይን እና ቁጥጥር ግን የራሱ መሆኑን ጠቁሟል። የየአከባቢው ማህበረሰብ በራሱ መንገድ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን እና የማያስፈልጋቸውን ልየታ እንደሚያከናውን የጠቆመው ፕሮግራሙ መንግስታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች እነዚሁን ተረጂዎች ዲጂታሊ በመመዝገብ በቀላሉ ለመለየት እንዲቻል እያደረጉ መሆኑንም ጠቁሟል። ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ማህበረሰቡ እንዲያየው የተረጂዎች ስም ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግ አስታውቆ ማህበረሰቡ መካተት ያልነበረበት ሰው ካለ ቅሬታ እንዲያቀርበ መካተት የሚገባው ሳይካተት ከቀረም አቤቱታውን ማቅረብ የሚያስችል ነው ብሏል። ቅሬታ ተቀባይ ኮሚቴዎች መመስረታቸውነ አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button