ዜናጤና

ዜና፡ ባለፉት 10 አመታት የትራኮማ የስርጭት ምጣኔ ከ28 በመቶ ወደ 12 በመቶ መቀነስ ቢቻልም የህብረተሰብ ጤና ስጋትነቱ አልጠፋም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26/2016 .ም፡ ባለፉት 10 አመታት የትራኮማ የስርጭት ምጣኔው ከ28 በመቶ ወደ 12 በመቶ መቀነስ ተችሏል ሲል የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

በሀገራችን የትራኮማ በሽታን ለመከላከል ብሎም ለማጥፋ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን እና እንደ ሀገር የትራኮማ በሽታን ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች የስርጭት ምጣኔው ከ28 በመቶ ወደ 12 በመቶ መቀነስ ማስቻሉን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ገለጹ።

በሽታው ለህብረተሰብ ጤና ስጋት መሆን በማይችልበት ደረጃ ጨርሶ ለማጥፋት፤ ከሰነድ ዝግጅት ጎን ለጎን ሁሉም ባድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ሚኒስትር ዴዔታው ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያሉት የተመዘገቡትን ውጤቶች በሰነድ መልክ ለማስቀመጥ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በአዲስ አባባ በተደረገ ውይይት ወቅት መሆኑን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በሽታው በህብረተሰቡ ጤና ላይ ዘርፈ ብዙ ጫናዎችን/ተግዳሮት ማሳደሩን በመጠቆም መንግስት ለጉዳዩ በሰጠው ልዩ ትኩረት፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ፣ በየደረጃው ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ የስርጭት ምጣኔው መቀነስ እንደተቻለም ገልፀዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ዴስክ አስተባባሪ አቶ ፍቅሬ ሰይፉ በበኩላቸው፣ ከ290 በላይ የሚሆኑ ወረዳዎች በሽታውን ከመቀነሳቸው የተነሳ የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት እደላ እዳቆሙም ገልፀዋል ያለው የሚኒስቴሩ መረጃ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በትራኮማ በሽታ ምክንያት የሚከሰተውን የዓይን ቆብ መቀልበስ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እንዳገኙም ተናግረዋል።

በሌላ ዜና ከአይን ጤና ጋር በተያያዘ በመላው ኢትዮጵያ በኮርኒያ ህመም የሚከሰት ዓይነ ስውርነት (Corneal Blindness) በመስፋፋት በርካታ ግለሰቦችን እና ማህበረሰቦችን እያዳረስ እንደሚገኝ የሚያሳይ ትረካ ማስነበባችን ይታወሳል። ይህ አስከፊ ህመም ዕይታን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን የሚያስከትለው፣ ነፃነትንና እድሎችን ማሳጣት እንዲሁም ሰዎች ከማህበረሰባቸው ጋር የሚያስተሳስራቸውን ወሳኝ ግንኙነቶችም ያቋርጣል። የቅርብ ጊዜ ብሔራዊ መረጃዎች ባለመኖራቸው ምክንያት ትክክለኛ ቁጥሩን በግልጽ ማወቅ ባይቻልም፣ በባለሙያዎች ግምት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ አስከፊ በሽታ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ይህንኑ ትረካ ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ https://addisstandard.com/Amharic/?p=2979

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button