ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ኢትዮጵያ በሸንገን ቪዛ አመልካቾች ቁጥር ከኬንያ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9/2016 .ም፡ ወደ 27 የአውሮፓ ሀገራት በህጋዊ መንገድ በመጓዝ መንቀሳቀስ የሚያስችለውን የሸንገን ቪዛ ለማግኘት ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2022 ካመለከቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች መካከል ኢትዮጵያውያን ከኬንያውያን በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ መቀመጣቸው ተገለጸ።

የሸንገን ቪዛ ለማግኘት በ2022 ያመለከቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 21ሺ 99 መሆኑን የተቋሙ ሸንገን ቪዛ ድረገጽ መረጃ አስታውቋል። ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከልም በከፍተኛ ቁጥር የተከለከሉት የኢትዮጵያ አመልካቾች መሆናቸውንም መረጃ አመላክቷል።

ኢትዮጵያውያን አመልካቾች የሸንገን ቪዛ ለማግኘት በሚያመለክቱበት ወቅት የሚያወጡት ወጪ በአማካኝ 710 ዩሮ መሆኑን የጠቀመው የድረገጹ መረጃ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት 2022 በአማካኝ ለቪዛ መጠየቂያ ኢትዮጵያውያኑ ያወጡት ወጪ አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊየን ዩሮ መሆኑን አስታውቋል።

ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በአንደኝነት የተቀመጠችው ኬንያ 48ሺ 892 ዜጎቿ የሸንገን ቪዛ ለማግኘት ማመልከታቸውን መረጃው ያሳያል። በአጠቃላይ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 153ሺ 757 የሚሆኑ ዜጎች የሸንገን ቪዛ ለማግኘት በ2022 መጠየቃቸውን ድረገጹ አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button