ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የአውሮፓ ህብረት በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እና የበርካታ ንፁሃን ግድያ አሳስቦኛል አለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24/ 2015 ዓ.ም፡- የአውሮፓ ህብረት በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት፣ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እና በርካታ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸው እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡

ህብረቱ በከፍተኛ ተወካዩ ጆስፍ ቦረል በኩል ትላንት ነሃሴ 23 ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ሪፖርቶች አመላክተዋል ብሏል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በመግለጫው፤ የንፁሃን ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ፣ እየተካሄደ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ግጭቱን እያከናወኑ ያሉት አካላት መካከል ውይይት እንዲደረግ፤ የአፍሪካ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረቡትን ጥሪ እኔም ተቀላቅያለው ሲል አስታውቋል፡፡

በፖለቲካዊ መረጋጋት ወደ ውይይት፣ እርቅ እና ሰላም የሚያመሩ ማንኛውንም ሂደቶችን ለመደገፍ ህብረቱ ዝግጁ መሆኑንም አክሎ ገልጧል፡፡ “ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተለለይም በመካሄድ ላይ ባለው የሀገራዊ ውይይት ሂደት ማዕቀፍ ውስጥ የውይይት መንገድን እንዲከተል እናሳስባለን” ብሏል፡፡

ከአውሮፓ ህብረት መግለጫ ቀደም ብሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ሪፖርት በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ከሐምሌ ወር ወዲህ 183 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል

ተመድ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሳቢያ በመላ ኢትዮጵያ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የሚያሳይ ሪፖርት እንደደረሰውም አስታውቋል፤ አብዘሃኛዎቹም የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች መሆናቸውን እና ለእስር የዳረጋቸውም ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል መሆኑን ገልጿል።

በአማራ ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ሲዘግቡ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውንና ታፍሰው የታሰሩትም ሰዎች መሰራተዊ ነገሮች ባልተሟሉባቸው ማጎሪያዎች ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በፋኖ ታጣቂዎች እና በሀገሪቱ መከላለከያ ሰራዊት መካከል የሚካሄደው ግጭት መጠናከሩ እና የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መታወጁም ተጨምሮበት በአማራ ክልል ሁኔታዎች እጅጉን እየተባባሱ ነው ሲል የተመደ ሪፖርት አመላክቷል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button