ፖለቲካ

ዜና: ሱዳን “እኔ ጋ ያሉ ስደተኞቻችሁን እንደምንከባከባቸው እናንተ ጋ ያሉ የእኔን ስደተኞች ልትንከባከቡልኝ ይገባል” ስትል ኢትዮጵያን አሳሰበች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2/2016 ዓ.ም፡- ከቀናት በፊት የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አዋድ አሊ መሃመድን በአዲስ አበባ በመገኘት ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መወያየታቸው ይታወሳል።

ጉብኝቱን አስመልክቶ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ውይይቱ መልስ ሚኒስትሩ ሁሴን አዋድ አሊ መሃመድን ሀገራቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ተንከባክባ እንዳስጠጋች በመግለጽ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የሱዳን ስደተኞች ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ተመሳሳይ እንክብካቤ እንደምትጠብቅ ማስገንዘባቸውን አስታውቋል።

ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አረጋ ጋር በመነበራቸው ውይይት እኛ ጋ ያሉ ስደተኞቻችሁን እንደምንከባከባቸው እናንተ ጋ ያሉ የእኛን ስደተኞች ልትንከባከቡልን ይገባል ሲሉ መናገራቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) ዘግቧል።

የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአምባሳደር ምስጋናው የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ማብራሪያ መስጠታቸውን እና የሱዳን ጎረቤት ሀገራት በሱዳን ሰላም ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና ገለጻ መስጠታቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት በዘገባው ጠቅሷል።

አምባሳደር መሀመድ ሁሴን ኢትዮጵያ በሱዳን ሁለንተናዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ውስጥ እየተጫወተችው ያለውን ሚና በማድነቅ በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ እና ወንድማማቻዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወሳኝ ሚናዋን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወሳል።

አምባሳደር ምስጋኑ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ረገድ እስካሁን የተጫወተችውን ሚና አውስተው አበርክቶዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል ሲሉ ዘገባዎቹ አትተዋል።

በውይይታቸው ወቅት አዲስ የተሾሙት በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ኤል ዘይን ኢብራሂም ሁሴን መገኘታቸውንም ሱና በዘገባው ጠቁሟል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button