ቢዝነስ

ዜና: የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ከስድስት አመታት በኋላ የአስተዳደር ርክክብ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ሲያስተዳድር የነበረው የቻይና ኮርፖሬሽን ከስድስት አመታት በኋላ የአስተዳደር ርክክብ ማካሄዱ ተገለጸ።

ላለፉት ስድስት አመታት የኢትዮ ጂቡቲ ባቡርን ሲያስተዳድር የነበረው የቻይና የሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የአስተዳደር ርክክብ መርሀ ግብር ማካሄዱን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በመርሀ ግብሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ፣ የጅቡቲ ትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሁመድ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በመርሀ ግብሩ የቁልፍ ርክክብ የተደረገ ሲሆን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ ከቻይናው የሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ተረክበዋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ቀጣናዊ ትስስርና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እንዲጎለብት ወሳኝ ሚናን የሚጫወት መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በርክክቡ ወቅት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና የሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጉኦ ቾንግ እንዳሉት፤ ባለፉት ስድስት አመታት በርካታ የልምድ ልውውጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠቱን አመላክተዋል።

በአጠቃላይ 2ሺህ 840 ሰዎች ሰልጥነው ሰርተፊኬት መውሰዳቸውንም ነው የገለጹት።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሰልጣኞቹም በጥገና በባቡር የፊልድ ኦፕሬሽን እና በባቡር ደህንነት በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ በበኩላቸው የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር መንፈስ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የንግድ ልውውጡን በማሳደግ የሁለቱን ሀገራት ቅርርብ ማጎልበቱን ጠቁመው፤ መሰረተ ልማቱ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢኮኖሚው ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ የባቡር መስመሩ ስኬታማ ስራ እና ጥገና ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

መሰረተ ልማቱ የትብብር እና የጋራ ምኞት ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ ወደብ ከሆነችው ጅቡቲ ጋር በማገናኘት ንግድ እንዲሳለጥ፣ የመጓጓዣ ጊዜ እንዲቀንስ እና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

ሸቀጦች የግብርና ምርቶች እና ማዕድኖች በቅልጥፍና እንዲጓጓዙ በማድረግ ኢኮኖሚው ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button