ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና: የፍትህ ሚኒስቴር የሽግግር ፍትህ ፓሊሲን ለማጸደቅ በቀጣይ ሳምንታት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20/2016 ዓ.ም፡- የፍትህ ሚኒስቴር በባለሞያዎች ቡድን አቋቁሞ ሲያዘጋጀው የነበረው የብሔራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ወደ ማጠናቀቂያው ምእራፍ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ በረቂቅ ብሄራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ላይ ያተኮሩ አራት የማጠናቀቂያ ምክክር መርሀ-ግብሮችን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ማካሄዱን በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ጠቁሟል።

በቀጣይ ቀናት በምክክር ድረኮቹ ወቅት ከተሳታፊዎች የተሰጡ እና በፅሁፍ የሚተላኩ ግብአቶችን በማየት እንደአግባብነቱ በፖሊሲው የመጨረሻ ረቂቅ ውስጥ የማካተት ስራ እንደሚያከናውን አስታውቋል።

የብሄራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው የመጨረሻ ረቂቅ ስራ እንደተጠናቀቀም ቀጣዩ ምዕራፍ ሰነዱን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በመላክ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በመንግስት እንዲፀድቅ ማድረግ ይሆናል ብላል።

ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያላቸው መርሃ ግብሮች ውስጥም የመጀመሪያው የካቲት 13/2016 ዓ.ም ከፖለቲካ ፓርቲ አራሮች ጋር ያካሄደው መጎኑን ጠቁሞ የካቲት 14/2016 ዓ.ም ደግሞ ከዲሞክራቲክ እና ሰብአዊ ብት ተቋማት ተወካዮች፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፡ የሚዲያ ባለሙያዎች፡ ምሁራን፡ የሽግግር ፍትህ ባለሙያዎች፡ የተመድ ኢትዮጵያ ፅህፈት ቤት ተወካዮች፡ እና የኤምባሲ ተወካዮች ጋር ማከናወኑን ገልጿል።

የካቲት 15/2016 ዓ.ም ከላው የሀገሪቱ ክፍሎች ከመጡ የህዝብ ወኪሎች፡ የመብት ጥሰት ተጎጂዎች፡ የሴቶች መብት ጠባቂዎች፡ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት፡ የህፃናትና ወጣቶች መብት ጠባቂዎች፡ እና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጋር መወያየቱን አስታውቆ አራተኛው ደግሞ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ከመንግስት የአስፈፃሚ፡ የፍትህ እና የጸጥታ መዋቅር ሀላፊዎች ጋር ምክክሮች ያከናወነው መሆኑን አመላክቷል።

የረቂቅ ፖሊሲውን ይዘት የሚያጠናክሩ፡ የሚተቹ ወይም ተጨማሪ አማራጮችን የሚያሳዩ ሀሳቦች በመድረኮቹ መቅረባቸውን አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button