ዜናፖለቲካ

ዜና: መንግስት በሊትር እስከ ስምንት ብር የሚደርስ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማድረጉ ተገለጸ፤ ባለሞያዎች የዋጋ ግሽበቱን ሊያባብስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29/2017 ዓ.ም፡- መንግስት በነዳች የችርቻሮ ዋጋ ላይ በሌትር እስከ ስምንት ብር የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉ ተገለጸ።

በሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ ነው ተብሎ የተገለጸው ጭማሪያው በሀገሪቱ የሚታየውን የዋጋ ግሽበት እንዳያባብሰው ስጋታቸውን ባለሞያዎች እና ሸማቾች ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

ከትላንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ቤንዚን በሌትር 91 ብር መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ናፍታ ደግሞ 90 ብር በሌትር እንደሚሸጥ ተተምኗል። የዋጋ ጭማሪው ከመደረጉ በፊት የአንድ ሊትር የቤንዚን ዋጋ በችርቻሮ 82 ብር ከ60 ሳብቲም፣ ናፍታ ደግሞ በሌትር 83 ብር ከ74 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሞያ የሆኑ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የተደረገው የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ በሀገሪቱ በመታየት ላይ ያለውን አሳሳቢ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ ሊያባብሰው ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተዋል።

“ከታሪክ እንዳየነው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ከዋጋ ግሽበት ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው” ሲሉ ጠቁመው “በቅርቡ በሀገሪቱ የተደረጉ የዋጋ ማሻሻያዎች በግሽበቱ ላይ ጫና ፈጥረው አልፈዋል” ሲሉ ገልጸዋል።

እንደ ማክሮ ኢኮኖሚስቱ ገለጻ፣ ነዳጅ ምግብ ነክ ባልሆኑ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ለውጥ የሚያስከትል መሆኑን በየወሩ ይፋ ከሚደረገው “ወሳኝ የኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ መረጃ መረዳት ይቻቻል ሲሉ አመላክተዋል።

“በሌሎች ሸቀጦች ላይ የሚኖረው ተዘዋዋሪ ተፅዕኖ ቀደም ሲል የነበረውን ከባድ የኑሮ ውድነት የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከማክሮ ኢኮኖሚስቱ በተጨማሪ ሀሳባቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ያጋሩ ሸማቾች በበኩላቸው በነዳጅ ችርቻሮ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ስጋት እንደፈጠረባቸው አስታውቀዋል።

የከባድ ጭነት መኪና ሹፌር መሆኑን የገለጸልን ዮሐንስ ዳንኤል አሁን ላይ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ወጪ እንደሚጨምር ይጠብቃል ብሎ ነግሮናል፤ “ለምሳሌ ከቢሾፈቱ ወደ ድሬዳዋ በኩንታል ስንጭነው የነበረው 330 ብር ሲሆን አሁን የተደረገውን የነዳጅ ጭማሪው የአንድ ኩንታል የጭነት ዋጋውን እስከ 400 ሊያደርሰው ይችላል ሲል ጠቁሟል።

መንግስ ያደረገው የነዳጅ የችርቻሮ ዋካ ማስተካከያውን በተመለከተ በትናንትናው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አማካሪ አህመድ ቱሳ በሁለት ምክንያቶች ማስተካከያው መደረጉን አስታውቀዋል፤ የአለም የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ እና በሀገሪቱ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ተመን።

እንደ አማካሪው ገለጻ “አሁን ካለው የውጭ ምንዛሪ አንጻር ነዳጅ ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ በማጓጓዝ የሚወጣው ወጪ በሊትር እስከ 120 ብር ሊደርስ ይችላል” ብለዋል።

በዚህ ረገድ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሁኔታ ያገናዘበና ሀገር አቀፍ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ታሳቢ ያደረገ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በገበያ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ያገናዘበ የዋጋ ማስተካከያ ስትራተጂ ተነድፎ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

በስትራተጂው መሠረትም መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የተሟላ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት በነጭ ናፍጣ ላይ 80 በመቶ ድጎማ እንዲሁም በቤንዚን ላይ 75 በመቶ ድጎማ የሚደረግ ይሆናል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button