ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በአማራ ክልል “ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር ተፈጽሟል” ሲል ኢሰመኮ ኮነነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27/2017 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ሰዎች ለሕግ አግባብ ውጭ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዛ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አስታወቀ፤ በማናቸውም ወቅት ቢሆን የሚፈጸም እስር ተገቢውን የሕግ እና የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ሊከተል ይገባል ሲልም አሳስቧል።

የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን እና መርሖችን ያልተከተሉ እስሮች በአፋጣኝ ሊቆሙ ይገባል ሲል ጠይቋል።

ኢሰመኮ ትላንት መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልልጎንደር እና ባሕር ዳር ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተፈጸሙት እስሮች “በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ትእዛዝ ያልተፈጸሙ፣ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ መሆናቸው አመላክቷል።

የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የሚዲያ እና የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ወደ ጊዜያዊ ማቆያዎች እየተወሰዱ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመኮ ከመካከላቸው ቋሚ የሕክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች መኖራቸውን ገልጿል።

በትጥቅ ግጭት እና በጸጥታ መደፍረስ ወቅትም ቢሆን ሲቪል ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያበቃ በቂ ሕጋዊ ምክንያት መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ማሳሰባቸው በመግለጫው አስታውቋል።

“የተወሰኑ ልዩ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በፍርድ ቤት የተሰጠ የመያዣና የብርበራ ትእዛዝ መኖሩን፣ በተያዙ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ማረጋገጥ ይገባል” ማለታቸውንም አካቷል።

ማንኛውም አካል በሲቪል ሰዎች እና በሲቪል ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከማድረስ እንዲሁም የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከሚያውክ ተግባር ሊቆጠብ እንደሚገባ አሳስቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

መንግስት በአማራ ክልል ያካሄደውን “የዘፈቀደ እስር በሀገሪቱ የህግ የበላይነት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸረሸረ መሆኑን ያሳያል” ሲል አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማውገዙን መዘገባችን ይታወሳል።

መንግስት በበኩሉ በአማራ ክልል ሕግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰድኩ ነው ሲል መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባህርዳር ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

በክልሉ በመካሄድ ላይ ስላለው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ እና የክልሉ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መንገሻ ፈንታው በጋራ በመሆን ነበር።

የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ “በክልሉ ሁከት እና ብጥብጥን ለማስቆም ከክልሉ መንግስት ጋር በመሆን ችግር በሚፈጥሩ የታጠቁ ሀይሎች እና በመንግስት መዋቅር ላይ በሚገኙ አካላት እርምጃ መወሰድ መጀመሩን” መግለጻቸውን በዘገባችን ተካቷል።

የኦፕሬሽኑ ዓላማ ሁከትን እና ብጥብጥን አስወግዶ ለክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላምን ማስፈን ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ “ሕግ የማስከበር ሂደቱ የሚቆመው የክልሉ ሰላም ሙሉ በሙሉ ሲረጋገጥ ነው” ብለዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button