ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ኤርትራ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመን ክስ አስተባበለች፣ ኢትዮጵያ ቀጣናውን "የከበቡት" ችግሮች "መፍለቂያ እና ማዕከል ናት" ስትል ኮንናለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12/2017 ዓ.ም፡- የኤርትራ መንግስት የማስታወቂያ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቅርብ አጋር የሆኑት ሙላቱ ተሾመ “ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ  በሁሉም ዋና ዋና ግጭቶች ውስጥ ተሳትፋለች እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ሊያባብስ በሚችል ድርጊት ተሰማርታለች” ሲሉ ያቀረቡትን ክስ ውድቅ በማድረግ መግለጫ አውጥቷል።

የኤርትራ መንግሥት የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል በኤክስ ገጻቸው ትላንት የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባስተላለፉት መልዕክት “የኢትዮጵያ ውስጣዊ ቀውሶች በአስመራ ላይ ሊላከኩ አይገባም” ሲሉ ገልጸው ኢትዮጵያ ቀጣናውን “የከበቡት” ችግሮች “መፍለቂያ እና ማዕከል ናት” ብለዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ርዕሰ-ብሔር ሙላቱ ተሾመ ውንጀላን “ድፍረት የተሞላበት እና በትክክል የጦርነት አጀንዳን ለመሸፋፈን የታሰበ” ሲሉ ገልጸውታል።

አክለውም ኤርትራ ዓለም አቀፍ መርሆችን እንደምታከብር እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት አስረድተዋል።

በተጨማሪም ኤርትራ ሁሌም ለቀጠናዊ ሰላም እና መረጋጋት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው “የኢትዮጵያ ችግሮች ከራሷ ውስጣዊ የፖለቲካ ሁኔታ የመነጩ እንጂ፣ ኤርትራን መወንጀል መፍትሄ አይሆንም” ሲሉ አብራርተዋል።

ኤርትራውያን ከጎርጎሮሳውያኑ 1998-2000 በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል የተካሄደውን ደም አፋሳሽ የድንበር ግጭት በተመለከተ “የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ግዛቶች በመያዙ ምክንያት የተፈጠረ” እንደሆነ ይከሳሉ።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በ2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔን መቀበላቸውን ሲገልጹ ተስተካክሎ ነበር።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይሁን እንጂ በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን አስከፊ ጦርነት የቋጨውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በሁለቱ ሃገራት መካከል ተሻሽሎ የነበረው ግንኙነት በድጋሚ ተቀዛቅዟል።

ስምምነቱ በጦርነቱ ወቅት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን በተመለከተ የኤርትራ ኃይሎች ተሳትፎ ያሳየ ሲሆን ኤርትራ ለኢትዮጵያ ወታደሮች መጠጊያ መስጠቷን በመግለጽ በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ አድርጋለች መባሉን አስተባብላለች።

በተጨማሪም ኤርትራ በፕሪቶሪያ ስምምነት ደስተኛ አለመሆኗ መገለጹን ውድቅ በማድረግ “ስምምነቱ የኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ነው” ብላለች።

እንዲሁም በኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች የኤርትራ ወታደሮች እንቅስቃሴ መቀጠሉን የሚገልጹትን ክሶች ውድቅ አድርገው “ኤርትራ ጣልቃ ለመግባት ፍላጎት የላትም” ሲሉ አክሏል።

በአማራ ክልል ግጭት ላይ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ “ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሚሊሺያ እያደራጁ ነው” ያሉትን በተመለከተ፣ “በቀጠናው ያሉት ችግሮች ሁሉ የሚመነጩት ከኢትዮጵያ ውስጥ ነው። መፍትሄውም ሌሎችን በመወንጀል ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት አለበት” ብለዋል።

መግለጫው በመጨረሻም፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው የባሕር በር ስምምነት ለተጨማሪ የአካባቢው ውጥረት ምክንያት እንደሆነ ገልጿል።

የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገብረመስቀል የኤክስ ጽሑፍ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ “ኢሳያስ አፈወርቂ በፕሪቶሪያው ስምምነት ደስተኛ አይደለም ሲሉ ከገለጡት የሕወሓት ቡድን ጋር ሕብረት አድርገዋል: የህወሐት አመራሮች ክፋፋልንም እየተጠቀሙበት ነው” ሲሉ ላቀረቡት ክስ ማስተባበያም ሆነ ምላሽ አልሰጠም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button