ዜና

ዜና፡ ኢትዮጵያ በብሪክስ ጥምረት ጥቅሟን የሚያስከብር ብሔራዊ ስትራቴጂክ እቅድ አዘጋጀች 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17/ 2016 ዓ/ም፦ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር ብሔራዊ ስትራቴጂክ እቅድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት መዘጋጀቱን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ፡፡ 

በትናንትናው ዕለት ትኩረቱን በግብርናና ቴክኖሎጂ ላይ ያደረገ በብሪክስ ጥምረት ማዕቀፍ ስር የኢትዮጵያና የሩሲያ የምሑራንና የተመራማሪዎች ጉባኤ ተካሂዷል፡፡

በጉባኤው የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ስራቴጂክ እቅድ ማውጣቱ የተጀመረው የብሪክስ አባል ለመሆን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት በሚደረግበት ወቅት ጀምሮ ነው ብለዋል፡፡ 

ወደ ብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ለመግባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን እየተጠናቀቀ የሚገኝ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር ብሔራዊ ስትራቴጂክ እቅድ ወጥቷል፤ ይህን ለማፅደቅ የመጨረሻውን ውሳኔ እየተጠበቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውጤታማ የሆነችባቸውን የስንዴ ምርትና የሌማት ትሩፋትን ይዛ ወደ ብሪክስ ጥምረት ትገባለች ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት የምትወስዳቸው ስትራቴጂ፣ ፕሮጀክቶችና መደጋገፎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዝግጅትና ፍላጎት ለማድመጥ የሩሲያ የባለሙያዎች ቡድን መጥቷል ያሉት ጃፋር፤ በብሪክስ የኢትዮጵያ ፍላጎቷ ምን እንደሆነ መረጃ መሰብሰቡን፤ እንዲሁም ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ትኩረት በምትሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመለየት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሞስኮ በሚካሄደው የማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ቅድሚያ በምትሰጣቸው የእድገት ጉዳዮችን ለመለየት የዝግጅት ጊዜ በመሆኑ ከብሪክስ አስፈላጊውን ጥቅም ለማግኘት ይረዳታል ነው ያሉት፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በብሪክስ ጥምረት ውስጥ የሩስያ የሙያተኞች ጉባኤ ኃላፊ ቪክቶሪያ ፓኖቫ (ፒኤችዲ) ጉባኤው የኢትዮጵያን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚጠቅምም ገልጸዋል።

ሩሲያ አሁን ያለውን ትብብር ለማስፋትና በብሪክስ ጥምረት ማዕቀፍ ውስጥ ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን ጠቁመው፤ ይህ ውይይት ሁለገብ ትብብርን ወደ አዲስ ከፍታ ለማሳደግ ትልቅ ተስፋ እንዳለው አስረድተዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button