ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጠ፣ መስፈርቶቹንም ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21/2016 .ም፡ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ የምደባ መስፈርቶችን ይፋ አድርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መስፈርት መሰረት አንድ ሺ ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ እንደሚካሄድ አስታውቋል።

የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ እንደሚጠቀም የጠቀመው ትምህርት ሚኒስቴር የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው አስታውቋል።

ከዩኒቨርሲቲ ምርጫ ጋር በተያያዘ የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስታውቆ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ መቅረባቸውን አመላክቶ የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን መደረጉን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገጹ ከምደባ ጋር በተያያዘ መስፈርቶቹን በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ጾታ፣ የትምህርት ቤት ተዋጽኦ፣ የውጤት ተዋጽኦ፣ ከወሊድ ጋር የተያያዘ ጉዳይ፣  ትክክለኛ የሕክምና ቦርድ ማስረጃዎች ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች (identical twins)፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች የመስፈርቱ አካል መሆናቸውንም በዝርዝሩ አካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button