ዜናጤና

ዜና፡ በኢትዮጵያ በኮሌራ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ400 በላይ መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ400 በላይ መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ የኮሌራ ወረርሽኝን ሊያስፋፋው ስለሚችል ጥንቃቄ ይደረግ ሲል ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።

የጎርፍ አደጋ መከሰት ከጀመረበት በጥቅምት ወር ብቻ በኮሌራ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በመስከረም ወር ከተመዘገበው የ12 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ያመላከተው የአለም የጤና ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ በጥቅምት ወር ብቻ በኮሌራ ወረርሽኝ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ28 ሺ በላይ መሆኑን ከነዚህ ውስጥም 404 የሚሆኑት መሞታቸውን አስታውቋል።

ከኮሌራ ጋር በተገና ኘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ያመላከተው ድርጅቱ የኮሌራ በሽታ የገዳይነቱ ምጣኔ በወሩ መጀመሪያ ከነበረበት 1 ነጥብ 37 በመቶ ወደ 1 ነጥብ 43 ከፍ ማለቱን ጠቁሟል።

የኮሌራ ወረርሽኝ የተዛመተባቸው ወረዳዎች ቁጥርም መጨመሩን ያስታወቀው ድርጅቱ በወሩ መጀመሪያ ወረርሽኙ ተስፋፍቶ የነበረው በ81 ወረዳዎች የነበረ ቢሆንም በወሩ መጨረሻ ግን የወረዳዎቹ ቁጥር 97 መድረሱን አመላክቷል። ኮሌራ በወረርሽኝ መልክ ተስፋፈቶባቸው ከነበረው 295 ወረዳዎች ውስጥ በ198 ወረዳዎች ላይ የተከሰተውን ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን የአለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button