ዜና

ዜና፡ በትግራይ ክልል 1700 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ወደመደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11/2016 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል 1700 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ወደመደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

በጤና ቢሮው የጤና ኤክስቴንሽንና ጤና ማስተዋወቅ ቡድን አስተባባሪ አቶ ሚካኤሌ ሐጎስ ከጦርነቱ  በፊት በክልሉ ሁለት ሺህ 500 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እንደነበሩ አስታውሰው፤ አሁን ላይ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ባለሙያዎች ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ መደረጉን ገልጸዋል።

ወደሥራቸው የተመለሱ በርካታ ባለሙያዎች የስነ-ልቦና አቅማቸውን የሚያሳድግና ቀድሞ ወደነበሩበት የሥራ መንፈስ መመለስ የሚያስችል ስልጠና ተሰጥቷል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እንደ አቶ ሚካኤሌ ገለጻ፤ የግብአትና ለፕሮግራሞቹ መንቀሳቀሻ የሚሆን በጀት እጥረት፣ ከስር የሚወጡ መረጃዎች አለመጠናከርና ሌሎች ክፍተቶች ስራወን ወደተፈለገው ደረጃ ለማድረስ ተግዳሮት የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡

የግብአት አቅርቦት ሲመቻች የተለያዩ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞችን በቅርቡ ወደሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ከሚገኙ የጤና ተቋማት መካከል በጦርነቱ ምክንያት 80 በመቶ የሚሆኑ የተለያዩ መጠን ያለው ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን አመላክተው፤ አፋጣኝ ድጋፍ በሚያስፈልግ ቦታዎች ባለሙያዎቹ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛል ብለዋል፡፡

በትምህርት ቤቶችና ሰዎች በብዛት ወደሚሰባሰብባቸው አካባቢዎች በመሄድ የሕክምና አገልግሎት እየቀረበ መሆኑን የገለጹት አቶ ሚካኤሌ፤ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ሕፃናት ልየታ የማድረግና ሕክምና የመስጠት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተጨማሪም ለወባ፣ ኮሌራና በሌሎች አፋጣኝ በሽታዎች ላይ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ በሽታዎቹን ለመግታት ባለመቻሉ ወደ መደበኛ የጤና አገልግሎት ሥራዎች ለመግባት ተጨማሪ አቅም ይጠይቃል ሲሉ አስረድተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button