ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ኦነግ ከአመራሩ በቴ ኦርጌሳ ጋር በተያያዘ በክልሉ መንግስት የሚካሄደው ምርመራ አሳስቦኛል አለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም፡- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ትላንት ሚያዚያ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከአመራሩ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ባወጣው መግለጫ በክልሉ መንግስት የሚካሄደው ምርመራ እንዳሳሰበው አስታውቋል።

“የመንግሰተ የጸጥታ መዋቅር ባህረያት እና አካሄድ በቀይ ሽብር መጀመሪያ ግዜያት ይታዩ የነበሩ ሁኔታዎች ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው” ሲል ገልጿል።

የበቴ ኦርጌሳ ግድያ በኦሮምያ ሰላማዊ ትግል ከመቸውም ግዜ በላይ አደጋ ላይ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው ያለው መግለጫው የኦሮምያ ክልል መንግስት ከግድያው ጋር በተያያዘ እያካሄድኩትነው ባለው ምርመራ ገና ከጅምሩ ተአማኒነት የጎደለው ተግባር እየፈጸመ ነው ሲል ተችሏል።

በክልሉ መንግስት በመካሄድ ላይ ያለው ምርመራ ገልልተኛ ላለመሆኑ፣ ማስረጃዎች በማጥፋት ላይ ስለመሆኑ፣ የተሳሳተ መረጃ በመንዛት እና የማስቀየስ ስራ እየተከናወነ ስለመሆኑ ተአማኒነት ያላቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል።

ከመረጃዎቹ መካከልም አንደኛ አባሉ በቴ ኦርጌሳ ከግድያው በፊት ከማረፊያው አበባ ግራዝማች ሆቴል በጸጥታ ሀይሎች መወሰዱን፤ ሁለተኛ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከሆቴሉ እየጎተቱ ሲወስዱት በከፍተኛ ሁኔታ እየደበደቡት እንደነበር፤ ሶስተኛ የአይን እማኝ ሊሆን የሚችለው የማረፊያ ሆቴሉ ጠባቂ መረጃ እንዳያወጣ በሚል እንዲሰወር ተደርጓል፣ ታግቷል አልያም ተገድሏል፤ አራተኛ  የታጠቁ የመንግስት የጸጥታ መለዮ ልብስ ያደረጉ ሰዎች በቴ ኡርጌሳን መኪና ላይ ሲጭኑት፣ ወደ ቆሻሻ መጣያ ቦታ ሲወስዱት እና ከመኪና አውርደው እጁን ወደ ኋላ በማሰር ብዙ ጥይት እንዳርከፈከፉበት የተመለከቱ የአከባቢው ምስክሮች እንደገለጹለት፤ አምስተኛ ከክልሉ መንግስትና ከገዢው የብልጽግና ፓርቲ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች እና ግለሰቦች ግድያው የቤተሰብ ጠብ ጋር በማገናኘት ለማሳነስ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ መገንዘቡን እና የኦሮምያ ክልል የምስራቅ ሸዋ ዞን የመቂ ከተማ ፖሊስ መርማሪ ቡድን ሚያዚያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ማቋቋሙን እና ከህግ እና ከኦሮሞ ባህል ያፈነገጠ ተግባር እያከናወን እንደሚገኝ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ያላቸው ሰዎች ለፓርቲው ሪፖርት እንዳደረሱት አስታውቋል።

ባለፉት አምስት አመታት በሰላማዊ መንገድ በፖለቲካ፣ ባህል እና ሰብአዊ መብት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎች አፈጻጸማቸው እንዲሁም በእነዚሁ ግድያዎቸ ላይ የተከናወኑ “ምርመራ ተብየዎች” አካሄዳቸውም ሆነ ከምርመራው በኋላ የታየ ፍትህ አለመኖሩ መንግስት ገለልተኛ እና ተአማኒ የሆነ መርመራ ያደርጋል የሚለው ላይ ማሳያ ናቸው ሲል ገልጿል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶቸ ሂዩማን ራይት ዎች፣ አምነስቲ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የመንግስታቱ ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የዲፕሎማሲው ማሀበረሰብ ገለልተኛ ምርመራ እንዲከናወን ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“የመንግሰተ የጸጥታ መዋቅር ባህረያት እና አካሄድ በቀይ ሽብር መጀመሪያ ግዜያት ይታዩ የነበሩ ሁኔታዎች ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው” ሲል ገልጿል።

የኦሮሞ ህዝብ ሁኔታዎችን በትኩረት አንዲከታተል ሲል ምክረ ሀሳቡን ያስቀመጠው የኦነግ መግለጫ የኦሮሞ ህዝብ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ መሪዎቹ እንዳይጎዱበት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ያጢን ብሏል።

ኢሰብአዊ ድርጊቶች ሊወገዙ ይገባል ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button