ዜና

ዜና፡ ከተጀመረ 13ኛ ዓመቱን የያዘው የዓባይ ግድብ ግንባታ ሙሉ ሥራው በቀጣይ ዓመት ያልቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9/ 2016 ዓ/ም፦ ከተጀመረ 13ኛ ዓመቱን የያዘው የዓባይ ግድብ የሲቪል ሥራው 99 በመቶ መጠናቀቁን እና ሙሉ ሥራው በቀጣይ ዓመት እንደሚያልቅ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ። 

የዓባይ ግድብ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታው በሰባት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገልጸዋል። 

ዋናው የግድቡ ክፍል 107 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት እንደሚይዝ የተናገሩት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ከዚህ ውስጥ አንድ በመቶው ሥራ ብቻ እንደሚቀር አስረድተዋል።

ኢንጂነር ክፍሌ እንዳስታወቁት፤ የግድቡ የኤሌክትሮ ሜካኒካል በተለይም የተርባይንና ጄኔሬተር ተከላ ሥራው 78 በመቶ ተጠናቋል።

እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሁለት ተርባይን ዩኒቶች በተለያዩ ጊዜያት መገጠማቸውን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ፤ ቀሪ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ተርባይኖች በቀጣይ ወራት ተራ በተራ እየገቡ ይገጠማሉ ብለዋል።

በበርካታ ፈተናዎችና ጫናዎች ሳይበገር ግንባታው የቀጠለው የግድብ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎቹን ተርባይኖች ሥራ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ሲሉ አስረድተዋል።

የግድብ የውሃ ማስተላለፊያ አሸንዳዎች ግንባታ ከ85 በመቶ በላይ መድረሱን ኢንጂነር ክፍሌ አመላክተው፤ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 95 በመቶ መድረሱን አስታውቀዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የግድብ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግንባታ በሰባት ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ቢሆንም፤ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይና ሙሉ የፕሮጀክቱ ሥራው በቀጣይ ዓመት ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ሲሉ ተናግረዋል።

አጠቃላይ ሥራዎችንም በ2017 ዓ.ም በማጠናቀቅ የመላው ኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነውን የዓባይ ግድብ ከፍጻሜው ለማድረስ አስፈላጊው ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button