ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳን አብዲ ኢሌ ክስ እንዲቋረጥ መደረጉ የወንጀል ተግባርን እንደማበረታታት የሚቆጠር ነው - ሂዩማን ራይት ዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9/2016 ዓ.ም፡- እጅግ የከፋ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ሞሃመድ ኦመር (አብዲ ኢሌ) ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጎ መፈታታቸው የወንጀል ተግባራን እንደማበረታታትና እውቅ እንደመስጠት ነው ሲል ሂዩማን ራይት ዎች ተቸ።

አብዲ ኢሌ ከአምስት አመታት እስር በኋላ ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ መደረጋቸው በወንጀል ተሳትፎ ያላቸውን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል ለሚደረገው ጥረት እንቅፋት ይሆናል ሲል አሳስቧል።

አብዲ ኢሌ ለእስር የተዳረጉት ሰብአዊ መብትን በመጣስ ወንጀል በመፈጸማቸው፣ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ግጭት እንዲፈጠር በማድረጋቸው መሆኑን ያወሳው ተቋሙ በተጫማሪም በስልጣን ዘመናቸው መገባደጃ ቀናት በክልል በሚኖሩ ሌሎች ብሔር ተወላጆች ላይ ታማኝ ሰራዊታቸው ልዩ ሀይል ጥቃት ሲፈጽም በነበራቸው አስተዋጽኦ መሆኑን አስታውቋል።

ከተመሰረተባቸው ክስም ውስጥ አብያተ ክርስቲያናት እንዲወድሙ መደረጋቸውን እንደሚገኝበት አስታውሷል።

በወቅቱ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው ተጠቂዎች የአብዲ ኢሌ ክስ ተቋርጧል መባሉ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ እና አሳዛኝ ዜና ነው ሲል ገልጿል።

በስልጣን ዘመኑ በፈጸማቸው በርካታ ወንጀሎች አብዲ ኢሌ እንዲጠየቅ ባለማድረጉ የኢትዮጵያ መንግስት አለመጠየቅ የዘመኑ አካሄድ ነው የሚል የተሳሳተ መልዕክት የሚያስተላለፍ ነው ሲል ተችቷል።

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ለመተግበር ሳምንታት ነው የቀሩኝ ለሚለው መንግስት የክስ ማቋረጡን ተግባር በመተው አሁንም ተጠያቂነት ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኑን ሊያሳይ ይገባል ሲል አሳስቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የቀድሞ የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት በክልሉ በስልጣን በቆዩባቸው ግዜያት የፈጸሙት ወንጀሎች ዙሪያ ክስ እንዳልተፈጸመባቸው በመግለጸ ሂዩማን ራይት ዎች ድርጊቱን ኮንኗል።

አብዲ ኢሌ የክልሉ የጸጥታ ሀላፊ ከነበሩበት ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ክልሉን ከ2002 ዓ.ም እስከ ታሰሩበት ቀን ድረስ በንጹሃን ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ተቋሙ ማቅረቡን አስታውቋል። ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ መፈጸም፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግርፋት እና በአከባቢው ማህበረሰብ ላይ ብቀላ መፈጸም የመሳሰሉ ወንጀሎች ተፈጽሟል ብሏል።

አብዲ ኢሌ በስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን የተፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ማውጣቱን ያሳታወቀው ተቋሙ በተለይ ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ.ም የሰብአዊ መብት ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት ላይ የክልሉ ልዩ ሀይል በኦጋዴን እስር ቤት ተፈጸሙ ያላቸውን  ወንጀሎች በዝርዝ ማቅረቡን ጠቁሟል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button